World News

ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ሂዝቦላ በእሳት እየተጫወተ ነው ሲሉ አስጠነቀቁ

አዲስ አበባ፣ሐምሌ 22፣ 2012 እስራኤል ሰሞኑን በድንበር አካባቢ ከሂዝቦላ ታጣቂዎች ጋር የተኩስ ልውውጥ ማድረጓንና የተቃጣባትን ጥቃት በብቃት መመለሷን ተናግራለች፡፡ኔታኒያሁ በሰጡት መግለጫ የሂዝቦላ ታጣቂ ቡድን ሉዓላዊ ድንበራችንን ጥሶ ለመግባት ሙከራ ማድረጉ በእሳት ጨዋታ መሆኑን ሊያውቅ ይባዋል ብለዋል፡፡ለሚቃጣብን ማንኛውም ጥቃት የምንሰጠው የአፀፋ ምላሽ የከፋ መሆኑን አውቆ ቡድኑ አደብ መግዛት አለበት ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስጠንቅቀዋል፡፡አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው በድንበር አካባቢ የተፈጠረው ውጥረት መነሻው ካሁን ቀደም እስራኤል ሶሪያ ውስጥ በሚገኘው የሂዝቦላ ጦር ሰፈር ላይ የሮኬት ጥቃት ማድረሷ ሳይሆን አይርም፡፡ሂዝቦላ በበኩሉ እስራኤል በኛ ላይ ዘመቻ እከፍታለሁ ብትል ልንፋለማት ዝግጁዎች ነን የሚል መግለጫ ሰጥቷል፡፡ የእስራኤል መከላከያ ሃይል ግጭቱ በተፈጠረበት ሊባኖስ፣ እስራኤል እና ሶሪያ የይገባኛል ጥያቄ በሚያነሱበት አካባቢ ያሉ ነዋሪዎች በተኩስ ልውውጡ ጉዳት እንዳይደርስባቸው በቤት ውስጥ  እንዲቀመጡ ትዛዝ ማስተላለፉን ገልጿል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button