World News

ሩሲያ የመጀመሪያውን የኮቪድ19 ክትባት ለዓለም አበረክታለሁ እያለች ነው

አዲስ አበባ፣ሐምሌ22፣ 2012 የሞስኮ ባለ ስልጣናት እንደሚሉት ከሆነ የኮሮናቫይረስን ክትባት ለመላው ዓለም ለማተዋወቅ ከሁለት ሳምንት ያነሰ ጊዜ ብቻ ነው የቀራቸው፡፡ጋማሊያ ኢንስቲትዩት አገኘሁት ያለውን ክትባት ቢበዛ እስከ ኦገስት 10 ባለው ጊዜ ወስጥ ይፋ አደርጋለሁ ብላለች ሩሲያ፡፡ይሁን እንጂ ሩሲያ ስለ ክትባቱ ሳይንሳዊ ማብራሪያ ከመስጠት መቆጠቧ የውጤታማነቱን ነገር ጥያቄ ውስጥ ይጥለዋል የሚሉ ወገኖች ስጋታቸውን ቀድመው እየገለፁ ነው፡፡ሲ ኤን ኤን የሩሲያ ተመራማሪዎችን ጠቅሶ እንደዘገበው ክትባቱ ከአሁን ለቀደም ለሌሎች በሽታዎች ታስቦ የተሰራውን በማሻሻል የሚዘጋጅ በመሆኑ ጊዜ አይወስድም ተብሎለታል፡፡ ክትባቱን የሚያዘጋጀው ተቋም ዳይሬክተር የሆኑት አሌክሳንደር ጊንስበርግ ድምፃቸው እንዲቀረፅ ፈቃደኛ በሆኑበት ቃለ ምልልስ ክትባቱን በራሳቸው ላይ እንደሞከሩት ነግረውኛል ብሏል ሲ ኤን ኤን፡፡ 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button