World News

በሊባኖስ የሟቾች ቁጥር ከ130 በላይ ሲደርስ የቆሰሉ ሰዎች ከ5 ሺህ በላይ መሆናቸው ተነግሯል::

አዲስ አበባ፣ሐምሌ30፣ 2012በሊባኖስ የሟቾች ቁጥር ከ130 በላይ ሲደርስ የቆሰሉ ሰዎች ከ5 ሺህ በላይ መሆናቸው ተነግሯል:: በወደብ ተከማችቶ በነበረ ኬሚካል ፍንዳታ ሳቢያ ከሞቱት እና ከቆሰሉት ሰዎች ባሻገር 300 ሺህ ሊባኖሳዊያን ቤት አልባ መሆናቸውን የሀገሪቱ ቴሌቭዥን ዘግቧል፡፡ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች አሁንም በህንፃዎች ፍርስረሾች ስር ተቀብረው የቀሩ ሰዎችን ለማግኘት ፍለጋቸውን አጠናክረው እንደቀጠሉ ናቸው፡፡

ሮይተርስ እንደዘገበው በተከሰተው ፍንዳታ ምክንያት ህይዎታቸውን ላጡ ዜጎች የሀገሪቱ መንግስት የሶስት ቀናት ሀዘን አውጇል፡፡መንግስት የአደጋውን መንስኤ ለማጣራት በጀመረው እንቅስቃሴ የተወሰኑ የወደቡ ባለ ስልጣናት ላይ የቁም እስር ትእዛዝ ማስተላለፉም ተሰምቷል፡፡ ከመንግስት ሰዎች ማረጋገጫ ባይሰጥበትም ፍንዳታው የተፈጠረው ኬሚካሉ የተከማቸበት መጋዘን ላይ የብየዳ ስራ ሲከናወን መሆኑን የሀገሪቱ ሚዲያዎች ዘግበውታል፡፡ መንግስት የአደጋውን መንስኤ በፍጥነት አጣርቶ ወንጀለኞችን ለፍርድ ለማቅረብ ቆርጦ መነሳቱን አስታውቋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button