Uncategorized

ደቡብ አፍሪካ የኮቪድ-19 ፈንድ ያላግባብ አባክነዋል በተባሉ ባለ ስልጠጣናት ላይ ምርመራ ልትጀምር ነው::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 22፣ 2012 ደቡብ አፍሪካ የኮቪድ-19 ፈንድ ያላግባብ አባክነዋል በተባሉ ባለ ስልጠጣናት ላይ ምርመራ ልትጀምር ነው:: የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ይፋ እንዳደረጉት ኮሮናቫይረስን መከላከል ለሚያስፈልጉ ወጭዎች የተመደበው ገንዘብ ለሙስና ተጋልጧል፡፡በመሆኑም ልዩ የምርምራ ግብረ ሃይል ተቋቁሞ እነዚህን ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የሚጠረጠሩ ባለ ስለጣናትን መርምሮ ለህግ እንዲያቀርብ አዘዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ለዚህ ለጭንቅ ጊዜ የተመደበን ገንዘብ ለራሱ ጥቅም የሚያውል ባለስልጣን ካለ እሱ ከሰውነት ይልቅ የአዳኝ አውሬ ባህርይን የተላበሰ መሆን አለበት ሲሉም ድርጊቱን በፅኑ አውግዘዋል፡፡ የሀገሪቱ የግምጃ ቤት ተቋም ይህንኑ በመፍራት ግዥዎች በልዩ ጥንቃቄ እንዲከወኑ የተለያዩ ህጎችና መመሪያዎችን ቢያወጣም ችግሩን መከላከል እንዳልቻለ ነው የሚነገረው፡፡ አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው ቫይረሱን ለመከላከል በተመደበው ገንዘብ ላይ ምዝበራው የተካሄደው በተለይ ህብረተቡን ለማንቃት በሚደረጉ የማስተማርና የቅስቀሳ ስራዎች ወቅት ነው ተብሎ ይታመናል፡፡ ደቡብ አፍሪካ በአሁኑ ወቅት ከ6 መቶ ሺህ በላይ ዜጎቿ በቫይረሱ የተያዙባት ሲሆን ከነዚህ መካከልም ከ13 ሺህ በላይ የሚሆኑት ህይዎታቸው አልፏል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button