EthiopiaSocial

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር  በስምንት ወራት ዉስጥ በወጪ ንግድ 1.64 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ተገኝቷል አለ፡፡

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር  በስምንት ወራት ዉስጥ በወጪ ንግድ 1.64 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ተገኝቷል አለ፡፡

በ2011 በጀት ዓመቱ ስምንት ወራት ከግብርና፣ ከማኑፋክቸሪንግ እና ከማዕድን ምርቶች ዘርፍ በአጠቃላይ 2.69 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ በአፈፃፀም የተመዘገበው 1.64 (61.02%) ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ነው፡፡

ይህ አፈፃፀም ከአምናው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወራት ከተገኘው 1.81 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ጋር ሲነፃፀር በ171.74 (9.48%) ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ቅናሽ አሳይቷል፡፡

በበጀት ዓመቱ በስምንት ወራት ከተያዘላቸው ዕቅድ በላይ አፈጻጸም ያስመዘገቡት የወጪ ምርት ጫት እና ታንታለም ብቻ ሲሆኑ የዕቅዱን ከ75% እስከ 99% ክንውን ያስመዘገቡ ምርቶች ባህርዛፍ እና የጥራጥሬ ሰብሎች ናቸው፡፡

ከተያዘላቸው ዕቅድ ከ50% እስከ 74% ክንውን ያስመዘገቡ ምርቶች እንደቅደም ተከተላቸው ኤልክትሪክ፣ ቡና፣ የቅባት እህሎች፣ ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት፣ አበባ፣ ኤሌክትሪክ፣ ሻይ ቅጠል፣ ስጋ እና አትክልትና ፍራፍሬ ናቸው፡፡

በሌላ በኩል ከተያዘው ዕቅድ አንጻር በውጭ ምንዛሪ ገቢ ከ50 በመቶ በታች ዝቅተኛ ገቢ ያስመዘገቡ የወጪ ንግድ ምርቶች እንደቅደም ተከተላቸው ቆዳና የቆዳ ውጤቶች፣ ወተትና የወተት ተዋፅኦ፣ ቅመማቅመም፣ ምግብ መጠጥና ፋርማቲስቲካል፣ ሰም፣ ሌሎች ማዕድናት፣ የተፈጥሮ ሙጫና ዕጣን፣ የስጋ ተረፈ ምርት፣ የኬሚካልና የኮንስትራክሽን ግብዓት፣ ማር፣ የቁም እንስሳት፣ ዓሳ፣ ወርቅ፣ የብርዕና አገዳ እህሎች እና ብረታ ብረት መሆናቸዉን ሚኒስቴሩ በላከልን መረጃ ገልጿል፡፡

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button