Ethiopia

ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ዳግም ትመህርት ለማስጀመር የሚያስችል ጉባዔ በጂማ ዩኒቨርሲቲ መካሄድ ጀመረ ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2013 ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ዳግም ትመህርት ለማስጀመር የሚያስችል ጉባዔ በጂማ ዩኒቨርሲቲ መካሄድ ጀመረ ::ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ዳግም ትመህርት ማስጀመር የሚቻልበት ሁኔታ ላይ የሚመክር ጉባዔ በጂማ ዩኒቨርሲቲ ተጀምሯል።

በጉባኤው ላይ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴርና የጤና ሚኒስቴር የስራ ሃላፊዎች፣ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶችና ሌሎች የሚመለከታቸዉ አካላት ተገኘተዋል።በጉባኤው ዩኒቨርሲቲዎች የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ ከተከሰተ ጀምሮ ወረርሽኙን ለመከላከል የሰሩትን ስራ በኤግዚብሽን አቅርበዋል።

ዩኒቨርሲቲዎቹ የሰሯቸውን ከአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ ጀምሮ እስከ አጋዥ የመተንፈሻ መሳሪያ ድረስ ስራዎች አቅርበዋል።ጉባኤው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በኮቪድ-19 ምክንያት አቋርጠውት የነበረውን ትምህርት ዳግም ለማስጀመር ውሳኔ ላይ ይደረሳል ተበሎ ይጠበቃል።ትምህርቱን ለመጀመር አማራጭ የመፍትሔ ሃሳቦች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግበትም ተገልጿል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button