Africa

የኮትዲቯር ህዝባዊ አመፅ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2013  የኮትዲቯር ተቃዋወች በፕሬዚዳንት አላሳኒ ኦታራ ላይ ህዝባዊ አመፅ እንዲቀሰቀስ ጥሪ አስተላለፈፉ::የተቃውሞው መነሻ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2010 ወደ ስልጣን የመጡት ኦታራ በ2015 ዳግም ተመርጠው ሀገሪቱን እያስተዳደሩ የሚገኙ ሲሆን አሁን ለሶስተኛ ጊዜ እወዳደራለሁ ማለታቸውን ህገ መንግስቱ አይፈቅድላቸውም የሚል ነው፡፡

በሀገሪቱ የብዙ ተቃዋሚ ፓርቲወች ስብስብና ዋነኛ የምርጫው ተቀናቃኝ ሆኖ የቀረበው ፓርቲ የኦታራ እንቅስቃሴ ህገ ወጥ በመሆኑ እንዳይወዳደሩ ጫና ለመፍጠር ተቃውሞው አስፈላጊ መሆኑን ገልጿል፡፡ በኮትዲቯር በመጭው የፈረንጆቹ ህዳር ወር ማብቂያ ላይ የሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አለመረጋጋት እየታየበት በመሆኑ ከአስር ዓመት በፊት በሀገሪቱ የተከሰተውን አይነት ግጭት እንዳያስከትል ከወዲሁ ስጋትን ፈጥሯል፡፡

አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው ካለፈው ወር ጀምሮ በፕሬዚንቱ ላይ በሚደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች የፀጥታ ሰዎች በወሰደዱት እርምጃ በርካታ ሰወች ህይወታቸው አልፏል፡፡ ይሁን እንጂ የሐገሪቱ ህገ መንግስታዊ መማክርትና የምርጫ ኮሚሽን ኦታራ ለሶስተኛ ጊዜ እንዲወዳሩ ፈቅዶላቸዋል፤ በአንፃሩ የቀድሞውን ፕሬዚዳንት ሎረን ባግቦን በወንጀል መከሰሳቸውን ምክንያትአድርጎ ከውድድር ውጭ አድርጓቸዋል፡፡ ተቃዋሚወቹ ከሚያነሱት ተቃውሞ አንዱ ይህን ያደረጉት የህገ መንግስታዊ መማክርትና የምርጫ ኮሚሽን መፍረስ አለባቸው የሚል ነው፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button