Uncategorized

ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ለፀጥታና ደህንነት አካላት የፀረ-ሽብር ሥልጠና ሰጠ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2013ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ለፀጥታና ደህንነት አካላት የፀረ-ሽብር ሥልጠና ሰጠ::ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ለፀጥታና ደህንነት አካላት ሽብርተኝነትን መከላከልና ማክሸፍ በሚያስችሉ ስልቶች ላይ ያጠነጠነ ስልጠና መስጠቱን ገልጿል።

ስልጠናው ከመከላከያ ሠራዊት፣ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ ከፌዴራልና ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽኖች፣ ከሪፐብሊካን ጋርድና ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ልዩ ኃይል ለተውጣጡ አመራሮችና አባላት ነው የተሰጠው።ሽብርተኝነትን መከላከልና ማክሸፍ፤ የሽብር ተልዕኮዎችንም አስቀድሞ ማወቅ የሚቻልበትን የመረጃ ሥራ በተመለከተ የንድፈ ሃሳብና የተግባር ሥልጠና ነው።

አል ቃይዳ፣ አይ.ኤስ እና አልሸባብ የሽብር ቡድኖች የኢትዮጵያና የአካባቢውን አገራት የሠላም፣ የትብብርና የልማት ማዕቀፍ ለማደናቀፍ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ለመግታትና ለማክሸፍ ያለመ ስልጠና መሆኑም ተገልጿል።

ሽብርተኝነት የደቀነውን ስጋት፤ አሸባሪዎች የሚጠቀሙበትን ስልት እንዲሁም የቀጣናውንና ዓለም አቀፋዊውን ነባራዊ ሁኔታ የዳሰሰ ሲሆን፤ ስጋቱን መመከት የሚያስችሉ ንድፈ ሃሳባዊና ተግባራዊ የመከላከያ ዘዴዎችንም አካቷል።የሽብር ጥቃቶች ቢፈጸሙ በቀላሉና በአነስተኛ ኪሳራ ማክሸፍ በሚያስችል ስልት ላይ ያተኮረ መሆኑም ተመልክቷል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button