Ethiopia

ጠ/ሚ ዐቢይ እና የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ በጅማ ዞን ጉብኝት አደረጉ፡፡

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2013 ጠ/ሚ ዐቢይ እና የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ በጅማ ዞን ጉብኝት አደረጉ፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የጅማ ዩኒቨርሲቲ የስራ እንቅስቃሴን ጎበብኝተዋል

መሪዎቹ ዩኒቨርሲቲው የሚያካሂዳቸውን የምርምርና የግንባታ እንቅስቃሴዎች መጎብኘታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።በተያያዘም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በጅማ ዞን ጎማ ወረዳ ቡናን ወደ ውጭ በመላክ ስኬታማ የሆነ አርሶ አደርን የቡና ማሳ ጎበኝተዋል፡፡

አርሶ አደር ሳቢቅ አባመጫ ቡናን በማሳቸው በማምረት በቀጥታ ለውጭ ገበያ በማቅረብ ስኬታማ የሆኑ አርሶ አደር ናቸው።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከጉብኝቱ በኋላ እንዳሉት እንደ ሌሎች ሰብሎች ሁሉ ቡናን ኩታ ገጠም በሆነ የግብርና ዘዴ በመጠቀም ምርታማ ለማድረግ ይሰራል።

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በበኩላቸው፣ በኢትዮጵያ የተመለከቱትን የቡና ግብርና ዘዴ በሃገራቸው ለመተግበር ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል።የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በኢትዮጵያ ለሶስት ቀናት የስራ ጉብኝት ለማድረግ ሰኞ ጠዋት ላይ ጅማ ከተማ በመግባት ነዉ ጉብኝታቸዉን የጀመሩት፡፡ ፕሬዚዳንቱ ጅማ አባ ጅፋር አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል።ከፕሬዚዳንቱ በተጨማሪ የኤርትራው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳልህ እና አማካሪያቸው የማነ ገብረዓብ ኢትዮጵያ ገብተዋል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button