Ethiopia

የህዳሴ ግድብ ግንባታ ከተጀመረ አንስቶ ከህብረተሰቡ በተደረገ ድጋፍ 14 ቢሊዮን ብር ማሰባሰብ መቻሉ ተገለፀ::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2013 የህዳሴ ግድብ ግንባታ ከተጀመረ አንስቶ ከህብረተሰቡ በተደረገ ድጋፍ 14 ቢሊዮን ብር ማሰባሰብ መቻሉ ተገለፀ:: የታላቁ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሄራዊ ምክር ቤት ይህን አስተዋፅዖ ላደረጉት ሁሉ ምስጋና አቅርቧል፡፡

ለተሰበሰበው ገንዘብ በሀገር ውስጥ ከሚኖሩ ኢትያጵዊያን በተጨማሪ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያን እና ትውለደ ኢትዮጵያን ተሳትፎም የጎላ ነበር ተብሏል፡፡ የድጋፍ ገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብሮች አንዱ በሆነው የ8100 አጭር የፅሁፍ መልእክት ደግሞ እስካሁን ከ52 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተገኝቷል፡፡ በተለይ ይሄኛው መንገድ ቦንድ መግዛት ለማይችሉ ዜጎች ባላቸው አቅም የገግድቡን ግንባታ ለመደገፍ ሁነኛ አማራጭ እንደበር ነው የተገለጸው፡፡

በ8100 አጭር የፅሁፍ መልእክት ለሚልኩ ሰዎች የተዘጋጀው የ2ኛ ዙር የሎተሪ እጣ አሸናፊ የታወቀ ሲሆን ለአሸናፊዋ ግለሰብም የዘመናዊ አውቶሚል ተበርክቷላታል፡፡ ለግድቡ ግንባታ ድጋፍ እንዲውል የአጭር የፅሁፍ መልእክት ፕሮገራም እንዲሳካ አስተዋፅ ላበረከቱ አካላትም ምስጋና እንደሚገባቸው ምክር ቤቱ ገልጿል፡፡

የግድቡ የግንባታ ሂደት 76 በመቶ መድረሱት የተናገሩት የህዳሴው ግድብ ብሄራዊ ምክር ቤት አባል ዶክተር ዮሃንስ በንቲ እስከ ግንባታው ፍፃሜ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ተሳትፏቸው እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button