Ethiopia

በህግ ማስከበር ዘመቻው ግዳጃቸውን በጀግንነት ለፈጸሙ የሰራዊቱ አባላት እውቅና እንደሚሰጥ ተገለጸ፡፡

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 13፣ 2013 በህግ ማስከበር ዘመቻው ግዳጃቸውን በጀግንነት ለፈጸሙ የሰራዊቱ አባላት እውቅና እንደሚሰጥ ተገለጸ፡፡ በትግራይ ክልል በተደረገው የህግ ማስከበር ዘመቻ ግዳጃቸውን በጀግንነት ለፈጸሙ የሰራዊቱ አባላት በየደረጃው እውቅና እንደሚሰጥ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ገለጹ። የክልል ልዩ ሃይሎች በየቦታው የነበራቸው አስተዋጽ ከፍተኛ መሆኑንም አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ እንዳስታወቁት፤ በዚህ የህግ ማስከበር ላይ የተሳተፉ የሰራዊቱ አባላት እንደየደረጃቸው የተለያዩ ሽልማቶችን የሚሸለሙ ይሆናል። ሜዳሊያ እና ማዕረግ የሚሸለሙ እንዲሁም ሌሎች የዕውቅና አሰጣጥ ሥነ ስርአቶችም የሚሰጡ ይሆናል። “ጀግኖች ይሸለማሉ ታሪካቸውም ተፅፎ ለትውልድ ይቀመጣል” ያሉት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ፤ እነዚህ ጀግኖች የሀገር ቅርስ ስለሆኑ እነሱን ማስተዋወቅ፣ መጠበቅና ማበረታታት ተገቢ ነው ሲሉም አስታውቀዋል።

እንደ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ ማብራሪያ፤ በዚህ የህግ ማስከበር ስራ ላይ የህዝቡ ተሳትፎ ከፍተኛ የነበረ ሲሆን፤ የአማራ ክልል፣ የኦሮሚያ ክልል፣ የአፋር፣ የሶማሌ እና ሌሎችም ክልሎች በተለያዩ መንገዶች ያደረጉት አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደነበር አብራርተዋል። የቆሰሉ የሰራዊቱ አባላት በአብዛኛው በአማራ ክልል ሆስፒታሎች ሲታከሙ መቆየታቸውን የገለጹት ጄኔራል ብርሃኑ፤ በክልሉ ያሉ ሆስፒታሎችና የህክምና መስጫ ተቋማት ለሰራዊቱ ክፍት እንዲሆኑ
በማድረግ አምቡላንስና የህክምና ባለሙያ መድበው ቁስለኞችን በሰፊው ማከማቸውንና ሪፈር የተባሉት ብቻ ወደማዕከል መምጣታቸውን አስታውቀዋል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button