World News

እስራኤል በሁለት ዓመት ውስጥ አራተኛ ምርጫ ማካሄዷ የግድ ሆኖባታል ተባለ::

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 14፣ 2013 እስራኤል በሁለት ዓመት ውስጥ አራተኛ ምርጫ ማካሄዷ የግድ ሆኖባታል ተባለ:: የጠቅላይ ሚንስትር ቤናሚን ኔታኒያሁና የአጣማሪያቸው ቤኒ ጋንትዝ የአንድነት መንግስት በገጠመው ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ድንገቴ ምርጫ የማካሄድ ግዴታ ውስጥ ገብቷል፡፡ ባለፉት ሳምንታት የሀገሪቱ ምክር ቤት ፈርሶ አዲስ ምርጫ ይካሄድ የሚል ሀሳብ በህግ አውጭ አባላት መቅረቡን ተከትሎ ፓርላማው ፈርሷል ነው የተባለው፡፡

አልጀዚራ እንደዘገበው ምርጫው ለመካሄዱ ዋናው ምክንያት ህዝቡ በኔታኒያሁ ላይ ከፍተኛ ቁጣ ስላነሳና የኔታኒያሁ መንግስት የአስተዳደር ጉድለት ስለበዛበት ነው፡፡ ኔታኒያሁ አራተኛው ምርጫ መካሄዱ እንደማይቀር በተረዱ ጊዜ ምርጫውን ሳንፈልገው አደንዲካሄድ ከተገደድን እንደምናሸንፍ አትጠራጠሩ በማለት ለደጋፊዎቻቸው ተስፋ ሰጥተዋል::

የጠቅላይ ሚኒስትር ቤናሚን ኔታኒያሁ ሊኩድ ፓርቲና የመከላከያ ሚኒስትሩ ቤኒ ጋንትዝ ብሉ ኤንድ ዋይት ፓርቲ በመካከላቸው መተማመን ከጠፋ ሰነባብቷል ነው የተባለው፡፡ ኔታኒያሁ ላይ ከፓርቲያው ውጭ ባቻ ሳይሆን በፓርቲያቸው ውስጥም ጫናው ስለበረታባቸው ነው ምክር ቤቱ ፈርሶ በመጭው ማርች ወር ምርጫ የሚካሄደው፡፡ የግድ ምርጫ ማካሄድ ያስፈለገብት ምክንያት አንድም ኔታኒያሁ በ2020 የሀገሪቱን በጀት ለማፅደቅና ፖለቲካዊ ስምምነቶችን ለማክበር ፈቃደኛ መሆን ስላልቻሉ ነው ብለዋል መጫው ምርጫ እንዲካሄድ ድምፃውን የሰጡ ፖለቲከኞች፡፡ ኔታኒያሁ በመጭው ምርጫም ቢሆን የቀኝ ፖለቲካ አራማጅ ከሆኑትና አዲስ ፓርቲ ካቋቋሙት ጌዲዮን ሳር ቀላል የማይባል ፈተና ይጠብቃቸዋል ነው የተባለው፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button