Ethiopia

ዶክተር ፋና ሀጎስ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾሙ::

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 7 ፣ 2013  ዶክተር ፋና ሀጎስ ብርሃኔ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾመዋል። ዶክተር ፋና ሀጎስ ብርሃኔ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በህግ ትምህርት የተቀበሉ ሲሆን ሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪያቸውን በደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ፍሪስቴትና ዋርዊክ ዩኒቨርሲቲ ተምረዋል፡፡

ትምህርታቸውን በመቀጠልም ኬኒያ ናይሮቢ ከሚገኘው የአፍሪካ ሳይንስ አካዳሚ ፖስት ዶክትሬት አግኝተዋል፡፡በትግራይ ክልል ፍትህ ቢሮ ዐቃቤ ህግ እንዲሁም በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ለ12 አመታት የህግ ትምህርት ክፍል ረዳት ፕሮፌሰር በመሆን አገልግለዋል። በተጨማሪም የስርዓተ ጾታ ጥናት ኢንስቲቲዩት ዳይሬክተርና የህግና ስነ-መንግስት ኮሌጅ ዲን በመሆን ማገልገላቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።

ሹመቱ ከጥቂት ዓመታት በፊት በዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ምንም ተሳትፎ ያልነበራቸውን የሴቶችን ተሳትፎ አንድ እርምጃ የሚያሳድግና ወጣት ኢትዮጵያውያንን የሚያነቃቃ እንደሆነ ይታመናል ተብሏል።ዶክተር ፋና በአሁኑ ጊዜ የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት በመሆን እያገለገሉ ነበር።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button