COVID-19HealthNews

በአዲስ አበባ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ያላደረጉ ሰዎችን ማሰር መጀመሩን ፖሊስ አስታወቀ ።

በአዲስ አበባ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ያላደረጉ ሰዎችን ማሰር መጀመሩን ፖሊስ አስታወቀ ።

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2012  የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን  እንዳለው በአስቸኳይ አዋጁ መሰረት ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ሁሉም ሰው የግድ መጠቀም ባለበት ሰዓት እንዲጠቀም ያስገድዳል።በዚህም መሰረት የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብልጭንብል ያላደረጉ ሰዎች በፖሊስ በመታሰር ላይ ናቸው።የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ኮማንደር ፋሲካ ፈንታ እንዳሉት አዋጁን እንድናስፈጽም በተሰጠን ስልጣን መሰረት ህግ የጣሱ ሰዎችን ሁሉ በማሰር ላይ ናቸዉ።ከዚህ በፊት በትራንስፖርት ታክሲዎች እና አውቶቡሶች ላይ የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ካላደረጉ አገልግሎት እንደማይሰጡ ቢገለጽም አሁን ግን በማንኛውም ቦታ ሲንቀሳቀሱ የተገኙ ሰዎችን ሁሉ እንደሚያስር ኮሚሽኑ ገልጿል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button