Ethiopia

የኦሮሚያ ክልል ለፋሲል ከነማ የ25 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ያደረገበት ሚስጥር ይፋ ሆነ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 19፣ 2013 በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ ክላስተር ሀላፊ የሆኑት አቶ አዲሱ አረጋ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ለፋሲል ከነማ የ25 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ያደረገበት ሚስጥር ይፋ አደረጉ፡፡ አቶ አዲሱ በፌስቡክ ገጻቸዉ ላይ እንደገለጹት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ለፋሲል ከነማ የ25 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ያደረገበት ሚስጥር መታሰቢያነት ከአመታት በፊት አምባገነኑ የወያኔ ቡድን በኦሮሞ ህዝብ ላይ ሲያደርሰዉ የነበረዉን ግፍ በመቃወም ‹‹ የኦሮሞ ደም የኔ ደም ነዉ! ›› በሚል ዉድ ህይወታቸዉ ለከፈሉ የጎነደር ወጣቶች ነዉ ብለዋል፡፡

በወቅቱ ወጣቶቹ ሳይሳሱ ታንክ እና መትረየስ ፊት ቆመዉ ለኦሮሞ ህዝብ እና ለኦሮሞ ወጣቶች ትግል ያላቸዉን አጋርነት በአደባባይ በጀግንነት ላሳዩት የጎንደር ወጣቶች ያለንን ታላቅ አክብሮት፣ ወንድማዊ አጋርነት እና ፍቅር ለመግለጽ ነዉ ክልሉ ድጋፍ ያደረገዉ ብለዋል ፡፡ ትናንት እናንተ ‹‹ደማችሁ ደማችን ነዉ ›› ብላችሁ ከህዝባችን ትግል ጎን ዉድ ህይወታችሁን ሳትሰስቱ ለቆማችሁ ጀግኖች የጎንደር ወጣቶች እኛ ደግሞ ‹‹ድላችሁ ድላችን ነዉ›› ብለን ደስታችሁን በመካፈላችን ትልቅ ደስታ ይሰማናል ብለዋል አቶ አዲሱ ፡፡ ዛሬም በአንድነት ቆመን የህዳሴ ግድባችንን እዉን እንደምናደርግ፣ ሀገራዊ ሉዓላዊነታችንን በጽናት እንደምናስከብር ምንም ጥርጥር እንደሌላቸዉ አቶ አዲሱ ገልጸዋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button