Ethiopia

ቦርዱ የድምጽ መስጫ ወረቀቶች እጥረት የገጠማቸውን የምርጫ ክልሎች ይፋ አደረገ::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 3፣ 2013 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተወሰኑ የምርጫ ክልሎች የድምጽ መስጫ ወረቀቶች እጥረት መከሰቱን አረጋግጫለሁ አለ፡፡ ቦርዱ ይህን ያለው በሎጀስቲክስ እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ባጋጠሙ ችግሮች ዙሪያ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት ባደረገው ውይይት ነው፡፡ የቦርዱ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ሪፖርታቸውን በዝርዝር ካቀረቡ በኋላ ከፓርቲዎች ጋር በችግሮቹና መፍትሄዎቻቸው ዙሪያ ሰፊ ውይይት አድርገዋል፡፡ የእጩዎችን ቁጥር መሰረት አድርጎ በተደረገው የገንዘብ ድጋፍ ወቅት ፓርቲዎች የእጩዎች ቁጥር ላይ ባቀረቡት አቤቱታ፣ እንዲሁም በድምጽ መስጫ ወረቀት እና በውጤት ማሳወቂያ ፎርሞች መካከል የማስታረቅ ስራ ሲሰራ መቆየቱንም አብራርተዋል፡፡

በዚህም መሰረት የቦርዱ ኦፕሬሽን ክፍል ባከናወነው ኦዲት 54 የምርጫ ክልሎች የድምጽ መስጫ ወረቀቶች ድጋሚ ህትመት የሚያስፈልጋቸው ሆነው ተገኝተዋል። የድምጽ መስጫ ወረቀቶች ድጋሚ ህትመት የሚያስፈልጋቸው ክልሎችም በአፋር፣ አማራ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ፣ ኦሮሚያ፣ ሶማሌና ድሬዳዋ የሚገኙ ናቸው፡፡ በነዚህ የምርጫ ክልሎች ድምጽ መስጫ ወረቀቶችን በድምጽ መስጫው ቀን ለማድረስ የሚደረገውን
ጥረት አስመልክቶ ፓርቲዎች ሃሳባቸውን ሰጥተዋል ፡፡

በውይይቱ ወቅትም የድጋሚ ህትመቱ በአገር ውስጥ የሚከናወንበት መንገድ ቢፈጠር፣ በአንዳንድ የምርጫ ክልሎች ደግሞ የጸጥታ ችግር ያጋጠመባቸው ቦታዎች ድምጽ በሚሰጡበት ወቅት አብረው የሚሰጡበት እድል ቢመቻች የሚሉ አማራጮች ቀርበዋል፡፡ በሌሎች ምርጫ ክልሎች የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ በተወሰነለት ቀን ሰኔ 14 ቀን የሚከናወን መሆኑን ተጨማሪ መረጃዎቸን ለፓርቲዎች እና ለመራጮች እንደሚሰጥም ቦርዱ አሳውቋል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button