Ethiopia

ምርጫው ዓለም አቀፍ መስፈርትን አያሟላም-ባልደራስ::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 18፣ 2013 ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ 6ኛው አገር አቀፍ ምርጫ ዝቅተኛውን ዓለም አቀፍ የምርጫ መስፈርት የማያሟላ ነው አለ፡፡ ፓርቲው በፌስቡክ ገፁ ላይ ባሰፈረው ፅሁፍ በተለያዩ ጊዜያት ሳይንሳዊ ጥናቶች አካሂጄ ነው እዚህ መደምደሚያ ላይ ደረስኩት ብሏል፡፡ ምርጫው ችግር እንዳለበት በማሳያነት ካቀረባቸው ምክንያቶች መካከል በድምፅ አሰጣጥ ወቅት የምርጫ አስፈፃሚዎች የገዢው ፓርቲ እንዲመረጥ የሚረዱ ገለፃዎችን ያደርጉ ነበር የሚለው
ይገኝበታል፡፡

በመራጮች ምዝገባ ወቅት ያልነበሩ አዳዲስ ንዑስ የምርጫ ጣቢያዎችን ከመክፈት በተጨማሪ የማይታወቁ የምርጫ ጣቢያዎች ተከፍተው ድምፅ እዲሰጥባቸው መደረጉም ሌላው ስህተት ነው ብሏል፡፡ በእያንዳንዱ የምርጫ ጣቢያ የመራጩ ቁጥር እየታወቀ በብዙ የምርጫ ጣቢያዎች የድምፅ መስጫ ወረቀቶች ከመራጮች ቁጥር እንዲያንስ ተደርጓል ያለው ፓርቲው ይህም ተዓማኒነቱን ጥያቄ ውስጥ ይጥለዋል ብሏል፡፡

በቅድመ ምርጫው ወቅት በርካታ ችግሮችን አስተውያለሁ ያለው ባልደራስ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ውጤት ይፋ ካደረገ በኋላ ከምርጫው ጋር በተያያዘ ዝርዝር ጉዳዮች ላይ መግለጫ የሚሰጥ መሆኑንም ገልጿል፡፡ ምርጫውን ነፃ፣ፍትሃዊ እና ዴሞክራሲያዊ ማድረግ ጠቀሜታው በሥልጣን ላይ ላለው መንግሥት እና ተወዳድረው ለማሸነፍ ለሚፎካከሩት ፓርቲዎች ብቻ ሳይሆን ለሚወክሉት ሕዝብ ጭምር ነው ሲል ፓርቲው በመግለጫው ጠቅሷል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button