Ethiopia

የቀጥታ በረራም ሆነ ከአውሮፕላን ላይ እርዳታ መጣል የሚለው ሀሳብ ተቀባይነት የላቸዉም::

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 8፣ 2013 ለትግራይ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ በቀጥታ በረራም ሆነ የሀገር ሉዓላዊነትን በሚጥስ ሌላ ተግባር የሚደረግ እንቅስቃሴ አይፈቀድም ተባለ:: የብሔራዊ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ በተለይ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት፤ በዓለም ምግብ ፕሮግራምና ሌሎች ዓለም አቀፍ የእርዳታ ተቋማት በኩል ምግብና ምግብ ነክ ያልሆነ የእርዳታ አቅርቦቶች በተገቢው መንገድ ወደ መቀሌ እንዲያጓጓዙ መንግስት ሁኔታዎችን አመቻችቷል።

መንግስት የዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅቶች የሚሰጡትን እርዳታ እንዳይስተጓጎልና በወቅቱ እንዲደርስ ሁኔታዎችን እያመቻቸ መሆኑን ያመለከቱት ኮሚሽነሩ፤ የዓለም የምግብ ፕሮግራምና ሌሎች ዓለምአቀፍ ተቋማት በቀጥታ በረራ በማድረግና ከአውሮፕላን ላይ በመጣል እርዳታውን የማቅረብ ጥያቄ እንዳላቸው አብራርተዋል። ሆኖም የቀጥታ በረራም ሆነ ከአውሮፕላን ላይ እርዳታ መጣል የሚለው ሀሳብ ተቀባይነት እንደሌለው ጠቁመዋል።

በተባበሩት መንግስታት ለሰብዓዊ ድጋፍ የአየር በረራ አገልግሎት እንዲፈቀድ ባቀረበው ጥያቄ መሰረት የሰው ኃይላቸውን ከአዲስ አበባ ወደ መቀሌ ይዘው እንዲሄዱ መፈቀዱን አስታውሰው፤ በማንኛውም ሁኔታ ልዩና የቀጥታ በረራ የሚባል ፈቃድ እንደሌለ ተናግረዋል። በአየር ትራንስፖርት እንዲጓጓዝ በማድረግ ሉዓላዊነትን የሚጥስ ድርጊት እንደማይፈቀድም ነው ኮሚሽነሩ የገለጹት። የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል የሰብዓዊ ዕርዳታ በወቅቱ እንዲደርስ 400ሺ ኩንታል የምግብ እህልና አልሚ ምግቦችን በመቀሌ በመጋዘን ማስቀመጡን የብሔራዊ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን መግለጹ ይታወሳል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button