EthiopiaHealthNewsPolitics

ምክር ቤቱ ምርጫ ቦርድ ጠቅላላ ምርጫን በተመለከተ ያቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ ለዝርዝር እይታ ለቋሚ ኮሚቴ መራ::

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 22፣ 2012 ምክር ቤቱ ምርጫ ቦርድ ጠቅላላ ምርጫን በተመለከተ ያቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ ለዝርዝር እይታ ለቋሚ ኮሚቴ መራ

የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የመሰብሰቢያ አደራሽ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባውም የተለያዩ ውሳኔዎችን መርምሮ አጽድቋል።ምክር ቤቱ በመደበኛ ስብሰባው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጠቅላላ ምርጫን በተመለከተ ያቀረበውን የውሳኔ ሐሳብን ተመልክቷል።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርትኳን ሚደቅሳ የጠቅላላ ምርጫን በተመለከተ ለምክር ቤቱ ማብራሪያ አቅርበዋል።የቦርዱ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርትኳን ሚደቅሳ ባቀረቡት የውሳኔ ሀሳብም በቦርዱ የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ የመራጮች ምዝገባ የሚጀምረው ከሚያዚያ 14 ቀን 2012 ዓ.ም ቢሆንም፤ በሀገሪቱ ውስጥ በተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሣቢያ በርካታ ህዝብዊ እንቅሰቃሴዎች የተገደቡ በመሆኑ የምርጫው ጊዜው በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ማካሄድ እንደማይቻል ገልጸዋል።

ወረርሽኙ በአለምና በአገራችን በመከሰቱ መንግስት ቅድሚያ ለሕዝብና ለሀገር በሚል በርካታ እርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል፤ ሲለሆነም ቦርዱም በዚህ ጊዜ ምርጫ ማካሄድ እንደማይቻል መግለጹን ተገቢነው ብለዋል።የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ፥ ቦርዱ ተጠሪነቱ ለምክር ቤቱ መሆኑንና የመጨረሻ ውሳኔም የምክር ቤቱ መሆኑን ጠቁመው የቀረበውን የመፍትሄ ሀሳብ ለድምጽ አቅርበዋል።በዚህም ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የጠቅላላ ምርጫን በተመለከተ ያቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ የመፍትሄ ሀሳብ እንዲያቀርብ ለህግ፣ ፍትህና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በ3 ተቃውሞ፣ በ7 ድምፀ ተአቅቦና በአብላጫ ድምጽ መርቶታል።

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button