Ethiopia

ሞት አፋፍ ላይ የሚገኘው ህወሃት ህጻናትን እንደ ሰብዓዊ ጋሻ መጠቀሙን ቀጥሏል ተባለ::

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 21፣ 2013  አሸባሪው ህወሃት በአፋር ክልል ፈንተ-ረሱ በከፈተው ጥቃት አሁንም ህጻናትን እንደ ሰብዓዊ ጋሻ እየተጠቀመ ይገኛል። የሃገር መከላከያ ሠራዊትና የክልሉ ልዩ ሃይል በግንባሩ እየወሰዱት ባለዉ እርምጃ ጅንታዉን ከአካባቢዉ የማጽዳት ዘመቻ ተጨማሪ ለውጊያ ያልደረሱ ታዳጊዎች ተይዘዋል።  በግንባሩ ህብረሰተቡን በማስተባበር ስራ ላይ የሚገኘዉ የክልሉ ማረሚያ ቤት ምክትል ኮሚሺነር አቶ መሀመድ አህመድ ለኢዜአ እንደተናገሩት የክልሉ ለዩ ሃይልና መከላከያ ሠራዊቱ በጁንታው ላይ እየወሠዱ ባለዉ የተቀናጀ አርምጃ አበረታች ድሎች እያስመዘገበ ነዉ።

“ይሁንና ሞት አፋፍ ላይ የሚገኘዉ የህወሃት አሸባሪ ጁንታ ቡድን እስትንፋሱን ለማራዘም ዛሬም ገና አጥንታቸዉ ያልጠነከረ የትግራይ ለጋ ህጻናትን የጦርነቱ ሰለባ እያደረገ ይገኛል”  በግንባሩ ባለፈዉ ሳምንት በርካታ ታዳጊዎች በጦርነቱ ውስጥ መያዛቸዉን የገለጹት አቶ መሀመድ ዛሬም ሌሎች ተጨማሪ ሕጻናት ታዳጊዎች በጦርነቱ መጠነኛ ጉዳት ደርሶባቸዉ በሰራዊቱ መያዛቸዉን ገልጸዋል።

ታዳጊዎቹም አሰገድደዉ ያመጧቸዉና በሃሺሽ አስክረዉ ወደ ጦርነት ያስገቧቸዉ እንደሆነ ገልጸዋል።  “ልጁቹም ሲመጡ ያለመሳሪያ እንደሆነና አለቆቻቸዉም ከመከላከያ ቀምተዉ መሳሪያ ይሰጧችኋል ብለዉ እንዳመጧቸዉም” አቶመሀመድ ገልጸዋል።  ታዳጊዎቹ በአካባቢዉ በሚገኝ ጤና ተቋም ጤና የህክሞና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል።

Tags
Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close