Ethiopia

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የሳይበር ጥቃቶችን የመከላከል አቅሙ ከ96 በመቶ በላይ መድረሱን አስታወቀ፡፡

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2014 የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የሳይበር ጥቃቶችን የመከላከል አቅሙ ከ96 በመቶ በላይ መድረሱን አስታወቀ፡፡
ኤጀንሲው መረጃውን ይፋ ያደረገው የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ ነው። የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሹመቴ ግዛው ኤጀንሲው የሳይበር ጥቃቶችን ቅድመ መከላከል፣ ጥቃት የደረሰባቸውን መልሶ ወደ ነበሩበት ስራ የመመለስ አቅሙ አድጓል ብለዋል።


ባለፉት ስድስት ወራት ከሶስት ሺ 400 በላይ የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች መደረጋቸውን ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል። ባለፉት ጊዚያት በባንኮች፣ በማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት፣ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች፣ በክልል ቢሮዎች፣ የትምህርትና የሚዲያ ተቋማት የሳይበር ጥቃት ኢላማ ተደርገው እንደነበርም ገልጸዋል። እንደ ዋና ዳይሬክተሩ ገለጻ በአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ከፍተኛ የሳይበር ጥቃት ሙከራ ተደርጎ የነበረ ቢሆንም ጉዳቱን ማስቀረት ተችሏል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button