Ethiopia

በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው የሚገኙ ታዳጊዎች የቡሄ በዓልን በማስመልከት ለህዳሴ ግድብ ገንዘብ አሰባሰቡ፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 13፣2013  በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው የሚገኙ ታዳጊ ኢትዮጵያዊያን የቡሄ በዓልን በማስመልከት ለታላቁ ህዳሴ ግድብ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም አካሄዱ በፕሮግራሙ ላይም በቡሄ ጭፈራ የታጀቡ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል፡፡ ታዳጊዎቹ ካስተላለፏቸዉ መልዕክቶች ውስጥ የግድቡ መጠናቀቅ ህጻናትና ታዳጊዎች ትምህርታቸውን በአግባቡ በመከታተል የተሻለ ሕይወት እንዲመሩ ያስችላቸዋል የሚለው ይገኝበታል፡፡ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው መረጃውን ያጋሩት በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍፁም አረጋ የሁሉም ታዳጊዎች ሕልም እንዲሳካ ሁሉም ዜጎች ለግድቡ ግንባታ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ በታዳጊዎቹ ስም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button