Ethiopia

ሶስተኛው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በኢትዮጵያ መከሰቱን የሚያሳይ ምልክት መታየቱን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለጹ።

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 18፣2013 ሶስተኛው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በኢትዮጵያ መከሰቱን የሚያሳይ ምልክት መታየቱን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለጹ። ዶክተር ሊያ ጉዳዩን አስመልክተው ዛሬ በሰጡት መግለጫ በኢትዮጵያ ባሳለፍነው ሳምንት ብቻ 5 ሺህ 547 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ተናግረዋል፡፡ በአንድ ቀን ውስጥ ከ1 ሺህ በላይ ሰዎች መያዛቸውን የገለጹት ሚኒስትሯ የወረርሽኙ መጠን ከዚህ በፊት ካለው በእጅጉ መጨመሩን ተናግረዋል።

የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በአሁኑ ሰዓት ቫይረሱ የሚገኝበት ሰው ቁጥር ምጣኔ በእጅጉ መጨመርም ሶስተኛው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በኢትዮጵያ መከሰቱን የሚያመላክት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ማህበረሰቡም ከዚህ በፊት የሚያደርገውን ጥንቃቄ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ሚኒስትሯ አሳስበዋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button