Uncategorized

በአሜሪካ ሕፃናት በዴልታ ኮቪድ 19 ቫይረስ እየተጠቁ መሆኑ በአሜሪካ ሕፃናት በኮቪድ 19 ቫይረስ እየተጠቁ መሆኑ ተጠቆመ፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 18፣2013 በአሜሪካ ሕፃናት በዴልታ ኮቪድ 19 ቫይረስ እየተጠቁ መሆኑ በአሜሪካ ሕፃናት በኮቪድ 19 ቫይረስ እየተጠቁ መሆኑ ተጠቆመ፡፡ የአሜሪካ ፔዲያትሪክስ አካዳሚ እና የሕፃናት ሆስፒታል ማሕበር ባወጡት ሪፖርት÷ ባሳለፍነው ሳምንት ብቻ በሀገሪቱ ወደ 94 ሺህ የሚጠጉ ሕፃናት በቫይረሱ ተጠቅተዋል ፡፡ ሉዚያና እና ፍሎሪዳ በርካታ በኮቪድ 19 ቫይረስ የተጠቁ ሕፃናት ሪፖርት የተደረገባቸው አካባቢዎች እንደሆኑም ተመላክቷል፡፡

በኒው ኦርሊያንስ የሕፃናት ሆስፒታል ውስጥ የሚሰራ ዶክተር ማርክ ክላይን ÷ በሆስፒታላቸው ውስጥ በኮሮና ቫይረስ ተጠቅተው ሊታከሙ ከሚሄዱ ሕፃናት ግማሽ ያህሉ እድሜያቸው ከ 2 ዓመት በታች ነው ብሏል፡፡ የተቀሩት በቫይረሱ የተጠቁና በሆስፒታሉ ለሕክምና የተገኙ ሕፃናት ደግሞ እድሜያቸው ከ 5 እስከ 10 ባለው ክልል ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውን ጠቁመው፥ በጣም ሕፃናት በመሆናቸው ክትባት ለመስጠት አስቸጋሪ እንዳደረገው ዶክተሩ ገልፀዋል፡፡ ወረርሽኙ ከተከሰተ ወዲህ እስካሁን ወደ 4 ነጥብ 3 ሚሊዮን የሚሆኑ ሕፃናት ቫይረሱ እንደተገኘባቸውና ቁጥሩም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻቀበ መሆኑን ነው ከሲጂቲ ኤን የተገኘው መረጃ የሚያመላክተው፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button