Africa

በደቡብ አፍሪካ የሥራ አጦች ቁጥር ከዓለም ከፍተኛ ነው ተባለ፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 19፣2013 በደቡብ አፍሪካ የሥራ አጦች ቁጥር ከዓለም ከፍተኛ ነው ተባለ፡፡በብሉምበርግ ቁጥጥር በሚደረግባቸው የ82 ሃገራት ዝርዝር ውስጥ በደቡብ አፍሪካ የሥራ አጦች ቁጥር በከፍተኛ መጠን እየጨመረ መሆኑን አልጄዚራ ዘግቧል፡፡ የሥራ አጥነት መጠኑ በሁለተኛው ሩብ ዓመት ከ32.6 በመቶ እስከ መጋቢት ባሉት ሦስት ወራት ድረስ ወደ 34.4 በመቶ ከፍ ማለቱን በፕሪቶሪያ የሚገኘው የደቡብ አፍሪካ ሰታትስቲክስ የመረጃ ተቋም ባወጣው መረጃ አስታውቋል።

በብሉምበርግ ጥናት ውስጥ ደግሞ የሶስት ኢኮኖሚስቶች ግምቶች አማካይ ደግሞ 33.2 በመቶ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ ሰፋ ባለው ትርጓሜ መሠረት ሥራ አጥነት፤ ለሥራ ብቁ የሆኑ ነገር ግን ሥራ የማይፈልጉ ሰዎችን የሚያጠቃልል ሲሆን ፤ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ከነበረበት 43.2 ወደ 44.4 በመቶ ከፍ ብሏል። መንግሥት የኮቪድ-19 ገደቦችን እያጠናከረ በመሆኑ በሦስተኛው ሩብ ዓመት ውስጥ የሥራ አጥነት ቁጥሩ የበለጠ ሊጨምር ይችላል ተብሏል። ባለፈው ዓመት 7 በመቶ የቀነሰውን ኢኮኖሚ ለማነቃቃት እንዳልተቻለ ዘገባው ጠቅሷል፡፡ የሥራ አጥነት ቁጥር እየጨመረ መምጣቱም የሕዝቡን የኢኮኖሚ አቅም ለማረጋጋት የሚደረገውን ጥረት የሚያወሳስበው ሲሆን ፤የእርዳታ እርምጃዎችን በማራዘም በሀገሪቱ ላይ ጫና ይፈጥራል የሚል ስጋትን ፈጥሯል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button