Africacrime

የተባበሩት መንግስታ ድርጅት በዲሞክራቲክ ኮንጎ ጥቃት የሚደርስባቸው ዜጎች ቁጥር መጨመሩ አሳስቦኛል አለ፡፡

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2012 የተባበሩት መንግስታ ድርጅት በዲሞክራቲክ ኮንጎ ጥቃት የሚደርስባቸው ዜጎች ቁጥር መጨመሩ አሳስቦኛል አለ፡፡ ድርጅቱ በሪፖርቱ እንደስታወቀው ባለፉት ስምንት ወራት ብቻ በሀገሪቱ ምስራቃዊ ግዛት 1 ሺህ 300 የሚሆኑ ንፁሃን ሰዎች መገደላቸው ታወቋል፡፡ በተለይ ኢቱሪ፣ ሰሜንና ደቡባዊ ኪቩ አካባቢዎች የጥቃቱ ሰለባ የሚሆኑ ዜጎች ቁጥራቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻቀበ ነው ተብሏል፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ቢሮ ሀላፊ ሚሼል ባቺሌት አሁን ያለው ሁኔታ በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ ወደ ጦር ወንጀል ሊያድግ እንደሚችል ስጋታቸውን ገልፀዋል፡፡ ምንም ባልታጠቁ ንፁሃን ሰዎች ላይ ይህን መሰል ዘግናኝ ጥቃት መድረሱን ስሰማ በጣም አዝኛለሁ ሁኔታውም አስደንግጦኛል ብለዋል ባቺሌት፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው በዲሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ ከሞቱት ሰዎች በተጨማሪ ከጥቃቱ ራሳቸውን  ለማዳን ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሰዎች ቤት ንብረታቸውን ጥለው ለመሰደድ ተገደዋል፡፡ ታጣቂዎቹ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ኖቬምበር 2019 የመንግስት ወታደሮች በሰሜናዊ ኪቩ ባደረጉት ዘመቻ በቀል ተነሳስተው በርካታ ጥቃቶችን እያደረሱ እንደሆነም ተነግሯል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button