Ethiopia

አዲስ የመንግሥት ተሿሚዎች ስራ ከመጀመራቸው በፊት ሃብት እንዲያስመዘግቡ የሚደረግ መሆኑን የፌዴራል የስነ-ምግባር እና ፀረሙስና ኮሚሽን አስታወቀ።

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2014 አዲስ የመንግሥት ተሿሚዎች ስራ ከመጀመራቸው በፊት ሃብት እንዲያስመዘግቡ የሚደረግ መሆኑን የፌዴራል የስነ-ምግባር እና ፀረሙስና ኮሚሽን አስታወቀ። ኮሚሽኑ በ2013 ዓ.ም የሃብት ምዝገባ አፈፃፀም እና የ2014 ዓ.ም እቅድን በተመለከተ ጋዜጣዊ
መግለጫ ሰጥቷል። የኮሚሽኑ የሃብት ማሳወቅ እና ምዝገባ ዳይሬክተር መስፍን በላይነህ፤ በተጠናቀቀው ዓመት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ የህዝብ ተመራጮች፣ የመንግስት ተሿሚዎች እና ሰራተኞች ሃብት አስመዝግበዋል።

በአመቱ የ705 ሃብት አስመዝጋቢዎች መረጃ ትክክለኛነት መረጋገጡንም ገልጸዋል። በኦሮሚያ፣ በሲዳማ፣ በደቡብ፣ በሀረሪ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የተሻለ አፈፃፀም እንደነበርም ጠቅሰዋል። በ2014 ዓ.ም በፌዴራልና በሁሉም ክልሎች ሙሉ በሙሉ የሃብት ምዝገባ ይደረጋል ብለዋል
ዳይሬክተሩ። አዲስ የመንግሥት ተሿሚዎች ስራ ከመጀመራቸው በፊት ሃብት እንዲያስመዘግቡ የሚደረግ መሆኑንም ተናግረዋል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button