Ethiopia

የአሜሪካ መንግስት ለኢትዮጵያ ከ3 መቶ ሺህ ባላይ የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን የኮቪድ -19 ክትባቶችን ለገሰ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2014 የአሜሪካ መንግስት ለኢትዮጵያ ከ3 መቶ ሺህ ባላይ የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን የኮቪድ -19 ክትባቶችን ለገሰ:: በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ እንዳስታወቀው አሁን የተለገሰው ክትባት አሜሪካ በቅርቡ ከለገሰችው 1ነጥብ 6 ሚሊዮን ዶዝ ተጨማሪ ሲሆን ፤ይህም ለአፍሪካ ቃል ከተገባው 25 ሚሊዮን ህይወት አዳኝ ክትባት አካል ነው ተብሏል፡፡

የአሜሪካ መንግስት የክትባቶችን ስርጭት በተመለከተ ከአፍሪካ ህብረትና ከአፍሪካ በሽታዎች መከላከልና ቁጥጥር ማእከል ጋር በቅርበት እንደሚሰራም ተገልጿል፡፡ እስካሁን ለኢትዮጵያ የተለገሰው 2 ሚሊዮን የሚጠጋ ክትባት አሜሪካ ክትባቱን ለአለም ለማጋራት ካላት ቁርጠኝነት የተነሳ ነው ብሏል ኤምባሲው፡፡
የዴልታ ቫይረስ በአፍሪካ መከሰት የክትባቱን ከምንግዜውም በላይ አስፈላጊነት እንደሚያጎላው የገለፀው ኤምባሲው “በጋራ በመስራት ቫይረሱን መከላከል እንደሚቻል በፅኑ እናምናለን “ብሏል፡፡ ፕሬዚዳንት ባይደን “ክትባቱን የምናጋራው ህይወትን ለመታደግ ነው ፣አለምን በማስተባበርም ወረርሽኙ
እንዲያከትም እንሰራለን ይህም የእኛ አርአያነትና እሴታችን ነው “ ማለታቸውን በመግለጫው ተመላክቷል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button