Ethiopia

ባለፉት ሁለት ወራት ብቻ ከ60 ሺህ በላይ ዜጎች ለመከላከያ ሠራዊቱ ደም በመለገስ አጋርነታቸውን ማሳየታቸው ተገለጸ፡፡

አዲስ አበባ፣መስከረም 11 2014 ባለፉት ሁለት ወራት ብቻ ከ60 ሺህ በላይ ዜጎች ለመከላከያ ሠራዊቱ ደም በመለገስ አጋርነታቸውን ማሳየታቸው ተገለጸ፡፡
የብሔራዊ ደም ባንከ አገልግሎት የህልውና ዘመቻውን ተከትሎ ደም የሚለግሱ ዜጎች ቁጥር መጨመሩም አስታውቋል። ይህም በሀገር አቀፍ ደረጃ ያለውን የደም ክምችት እጥረት በመቅረፍ ረገድ ጉልህ አስተዋጽኦ ማድረጉን ነው የመከላከያ እና ብሔራዊ የደም ባንክ አገልግሎቶች የገለጹት።

የብሔራዊ ደም ባንክ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ያረጋል ባንቴ በበኩላቸው፤ የህግ ማስከበር ዘመቻው ከተጀመረ ጀምሮ የደም ለጋሾች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ  መጨመሩን ተናግረዋል፡፡ በተለይ የህግ ማስከበር ዘመቻ ከተጀመረበት ህዳር ወር ጀምሮ ህብረተሰቡ ደም በመለገስ ረገድ እያሳየ
ያለው ተሳትፎ አበረታች መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

ኢትዮጵያውያን አንድነታቸውን ጠብቀው አሸባሪው ህወሃት ሀገር ለማፍረስ እያከናወነ ያለውን ተግባር በመመከት ረገድ አኩሪ ታሪክ እየጻፉ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡ ዜጎች የመከላከያ ሠራዊቱን ከመቀላቀል ባሻገር ለሠራዊቱ የሚሆን የቁሳቁስ ድጋፍ እያደረጉ ሲሆን በአሸባሪ ቡድኑ ወረራ ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖችም ድጋፍ በማድረግ አለኝታነታቸውን በተግባር እየገለጹ ነው ተብሏል። ህብረተሰቡ ለሀገሩና ለወገኑ ህይወቱን አሳልፎ እየሰጠ ለሚገኘው ሠራዊት ደም የመለገሱን ተግባር አጠናክሮ እንዲቀጥል  ጥሪቀርቧል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button