Ethiopia

የአሜሪካ የማዕቀብ ይጣል ፕሬዚዳንታዊ ትእዛዝ ዓላማው አዲሱን የመንግሥት ምስረታ ማደናቀፍ ነው ሲሉ አምባሳደርና ጋዜጠኛ ተፈራ ሻወል ተናገሩ፡፡

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2014 የአሜሪካ የማዕቀብ ይጣል ፕሬዚዳንታዊ ትእዛዝ ዓላማው አዲሱን የመንግሥት ምስረታ ማደናቀፍ ነው ሲሉ አምባሳደርና ጋዜጠኛ ተፈራ ሻወል ተናገሩ፡፡አምባሳደርና ጋዜጠኛ ተፈራ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የአሜሪካ የማዕቀብ ይጣል ፕሬዚዳንታዊ ትእዛዝ የኢትዮጵያ መስከረም 24 ቀን 2014 የሚያካሂደውን የመንግሥት ምስረታ ማደናቀፍ፣ ስልጣን ለአሸባሪው ህወሓት ማጋራት ያም ካልሆነ ጦርነቱ ቆሞ አሽከሮቹ ነፍሳቸውን
አድነው ለመውጣት የሚያደርጉትን ጥረት ማሳካት ነው፡፡

ይህ አካሄድ በህጉ መሰረት ተቀባይነት የለውም፤ ወንጀለኝነት የሚያሳስርና የሚያስቀጣ ነው። አልሸባብ ወንጀለኛ ነው ብለን ከአሜሪካ ጋር በጋራ ሱማሊያ ውስጥ ስንዋጋ ነበር፤ በኢትዮጵያ በህግ ሽብርተኛ ነው ተብሎ በአሸባሪነት የተፈረጀውና የሚፈለገው አካል ሲታደን አሜሪካ የምታሳየው ሁኔታ ተገቢነት
የለውም ሲሉ አምባሳደር ተፈራ ተናግረዋል። የአሜሪካ አካሄድ ተአማኒነትም፤ ጽናትም የሌለው አካሄድ ነው በማለት የጠቆሙት አምባሳደሩ ፤ የምንሄድበትን አላማ እስካወቅን፣ የሕዝቡ አንድነትና ድጋፍ እስካለ ድረስ ካሰብንበት የሚያስቀረን ኃይል እንደማይኖርና የወደፊቱ የኢትዮጵያ ዕድልም ብሩህ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button