Ethiopia

ወራሪውና አሸባሪው ህወሓት በከፈተው ጦርነት 18 ሺህ 9 መቶ ኢንተርፕራይዞች መውደማቸው ተገለፀ።

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2014 ወራሪውና አሸባሪው ህወሓት በከፈተው ጦርነት 18 ሺህ 9 መቶ ኢንተርፕራይዞች መውደማቸው ተገለፀ።
በርዕስ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል ማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ ዶ/ር ሙሉነሽ አበበ እንደገለፁት የሽብር ቡድኑ በግፍ በከፈተው ጦርነት ሳቢያ በአማራ ክልል 18 ሺሕ 9 መቶ ኢንተርፕራይዞች ወድመዋል።

ለበርካታ ዓመታት ተደክሞባቸው የተገነቡ 23 የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆችም በጦርነቱ ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን ገልፀዋል። የሥራ ዕድል ፈጠራ የ2014 ዕቅድ ሲወጣ ወቅታዊ ሁኔታውን ያገነዘበና ከሥራ የተፈናቀሉ ተቋማትን ወደ ሥራ እንዲገቡ ማድረግ ሊተኮርብት እንደሚገባ ከዋልታ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button