Ethiopia

ከተ.መ.ድ. ጋር በአጋርነት ለመስራት ተዘጋጅተናል-አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2014 የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋምና መሰረታዊ ልማቶችን መልሶ ለመገንባት ከመንግስታቱ ድርጅት ጋር ለመስራት ዝግጁ ነው ተባለ፡፡ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን በኒውዮርክ የስራ ቆይታቸው ጎን ለጎን ከተመድ ምክትል ዋና ፀሃፊ አሚና ጄኔ መሐመድ ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል፡፡ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በፀጥታ ችግር ምክንያት የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም እና
የወደሙ መሰረታዊ አገልግሎቶችን መልሶ ለመገንባት መንግስት ከድርጅቱ ጋር በላቀ አጋርነት ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ነው አቶ ደመቀ የተናሩት፡፡

በመሆኑም መንግስት በመልሶ ማቋቋም እና በመልሶ ማልማት ተግባራዊ እንቅስቃሴ ሂደት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ከተባበሩት መንግስታት ይሰራል ብለዋል፡፡ በዘላቂ ልማት ግቦች አፈፃፀም፣ በሰብዓዊ አገልግሎት ድጋፍ አሰጣጥ እና ወቅታዊ የሃገር ውስጥ ጉዳዮችን በተመለከተም በዝርዝር መወያየታቸውን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ በአሁን ጊዜ ሃገራችንን እየገጠሟት ካሉት የፀጥታ ችግሮች ጋር በተያያዘ የመልሶ ማቋቋም እና የመልሶ ማልማት ተልዕኮን ለማስፈፀም በተመድ በኩል የበለጠ ትብብር እና ድጋፍ እንጠብቃለን ብለዋል አቶ ደመቀ። እስካሁን ድረስ ተመድ በልማት እና ሰብዓዊ ድጋፍ አገልግሎት ዙሪያ ለኢትዮጵያ ላበረከተው አስተዋፅዖ በማመስገን በተለይ በዚህ ጊዜ የተሻለ ትብብርና መደጋገፍ እንደሚጠይቅ አቶ ደመቀ አስገንዝበዋል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button