Africa

 25ሺህ ያህል የኤርትራ ስደተኞች በአሁኑ ወቅት ያሉበት ሁኔታ አይታወቅም::

25ሺህ ያህል የኤርትራ ስደተኞች በአሁኑ ወቅት ያሉበት ሁኔታ አይታወቅም::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 04፣ 2014በአዲ-ሃሩሽና ማይ-አይኒ ጊዜያዊ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎች ይኖሩ የነበሩ 25ሺህ ያህል የኤርትራ ስደተኞች በአሁኑ ወቅት ያሉበት ሁኔታ አይታወቅም ተባለ። ከአሸባሪው ህወሓት ጥቃት ያመለጡ 244 የኤርትራ ስደተኞች በዳባት ጊዜያዊ መጠለያ አገልግሎት እያገኙ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት እንዳስታወቀው፤ ለስደተኞች የሚያገለግሉ 40 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ከተማ አቅራቢያ በተቋቋመው አለምዋጭ የስደተኞች ጣቢያ እየተገነቡ እንደሚገኙም አገልግሎቱ ገልጿል።

በስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት የማይጸምሪ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ጊዚያዊ አስተባባሪ አቶ ስንታየሁ በሪሁን ለኢዜአ እንደተናገሩት አዲ-ሃሩሽና ማይ-አይኒ ጊዜያዊ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎች ይኖሩ የነበሩ 25ሺህ ያህል የኤርትራ ስደተኞች በአሁኑ ወቅት ያሉበት ሁኔታ አይታወቅም። አሸባሪው ቡድን በመጠለያዎቹ ላይ በፈጸመው ዝርፊያና ወረራ ጉዳት መድረሱን ጠቁመው፤ ስደተኞችም መበታተናቸውንና አንዳንዶቹም እርዳታው በመቆሙ ለልመና መዳረጋቸውን ተናግረዋል። በተጨማሪም ስደተኞቹ የህክምና ድጋፍ እንደማያገኙና አንዳንዶቹም በሽብር ቡድኑ ታፍነው ወዳልታወቀ
ሥፍራ ስለመወሰዳቸው መረጃዎች መድረሳቸውን ገልጸዋል። የሽብር ቡድኑ በሁለቱ መጠለያ ጣቢያዎች መድፎችና ሌሎች ከባድ መሳሪያዎችን እንደተጠመደባቸውና ስደተኞቹንም መሳሪያዎቹን እንዲያጓጉዙ በማስገደድ ላይ እንደሚገኝ አቶ ስንታየሁ አስታውቀዋል።

በሰሜን ጎንደር ዞን የዳባት ወረዳ አስተዳደር በነጻ በተሰጠ 91 ሔክታር መሬት ላይ በተቋቋመው “አለምዋጭ” የኤርትራ የስደተኞች መጠለያ ላይ በ40 ሚሊዮን ብር በጀት የጋራ መኖሪያ ቤቶች እየተገነቡ ይገኛሉ። እያንዳንዳቸው 100 ስደተኞችን እንዲያስተናግዱ ተደርገው እየተገነቡ ካሉት 40 ቤቶች መካከል 15 ያክሉ ግንባታቸው እየተጠናቀቀ መሆኑን አቶ ስንታየሁ አስረድተዋል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button