Ethiopia

በአዲስ አበባ ከተማ እየተሰሩ ያሉ ፕሮጀክቶችን በተመለከተ መረጃዎችን ማግኘትና ሀሳብ መስጠት የሚቻልበት የኪነ ህንጻ እና ከተማ ማእከል ተከፈተ።

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2012  በአዲስ አበባ ከተማ እየተሰሩ ያሉ ፕሮጀክቶችን በተመለከተ መረጃዎችን ማግኘትና ሀሳብ መስጠት የሚቻልበት የኪነ ህንጻ እና ከተማ ማእከል ተከፈተ።ማእከሉ መስቀል አደባባይ ፊትለፊት ላይ የተዘጋጀ ሲሆን የካፌ አገልግሎትና ዋይፋይ የተዘጋጀለት ነው። በማእከሉ የትኛውም ዜጋ ስለከተማዋ እቅዶችና ፕሮጀክቶች መመልከትና የራሱን ሀሳብ በፅሁፍና በድምፅ መስጠት ይችላል። የተሰጡት አስተያየቶች በቦታው የሚገኙ ባለሙያዎች በማሰባሰብ ለከንቲባው በየጊዜው የሚያቀርቡ ይሆናል። የማእከሉ መቋቋም የከተማዋ ነዋሪ በከተማዋ ላይ ያለው ተሳትፎ እንዲጨምርና ስለ ከተማዋ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች ላይ ግንዛቤ እንዲፈጠርና ግልፅነት ለመፍጠር ያለመ ነው።

ምንጭ ፤- ከንቲባ ጽ/ቤት

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button