FACT CHECK

ሐሰት: የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ርዕስቱ ይርዳው ፌዴራል መንግሥት ጫና ያደርግብናል አላሉም።

የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ርዕስቱ ይርዳው ከወላይታ ህዝብ የክልልነት ጥያቄም ጋር ተያይዞ የፌዴራል መንግሥት ጫና ማድረጉን የሚገልጽ መግለጫ አልሰጡም።

የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ርዕስቱ ይርዳው “የወላይታ ጥያቄ እጅግ በጣም እያሳሰበኝ ነው” ብለዋል የሚለው የፌስቡክ ልጥፍ ሐሰተኛ ነው።

በአማርኛ የተጻፈው ልጥፍ  “#ሰበር #ዜና #የደቡብ #ክልል #ርዕስ #መስተዳድር

#አቶ #ርዕስቱ #ስለ #ወላይታ #እውነታውን #ተናገሩ

“ሆኖም የወላይታ ጥያቄ ተገቢ እና ሕገመንግሥቱን ያማከለ ነው እስካሁን ድረስ የወላይታ ሕዝብ የመጣባቸው መንገዶች ፍፁም ሰላማዊና ሕገመንግሥታዊ አካሄድ ነው:: በዚህ አካሄድ እጅግ በጣም ሊደነቅ የሚገባ ሕዝብ ነው:: ግን እኛ አንዳች ወሳኔ እንዳንሰጥ ፌዴራል መንግሥት ጫና ያደርግብናል”  የሚል ይዘት አለው ። 

የወላይታ ሕዝብ ባለፉት አመታት ካነሳቸው ጥያቄዎች የወላይታ ክልል የመሆን ጥያቄ ዋነኛው ተደርጎ ሊጠቀስ ይችላል። ግንቦት 9 ቀን 2011 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከተማ ክልል የመሆን ጥያቄያቸው በአፋጣኝ ምላሽ እንዲያገኝ ግፊት ለማድረግ ያካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ ይጠቀሳል።

የወላይታ ዞን በክልል የመደራጀት ጥያቄን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከወላይታ ሕዝብ ተወካዮች ጋር ሕዳር 21/2012 ዓ.ም በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል። ይሁንና እስካሁን የክልልነት ጥያቄው መልስ ባለማግኘቱ የወላይታ ህዝብ ክልል የመሆን ጥያቄው ምላሽ እንዲያገኝ ግፊት በማድረግ ላይ ይገኛል።

የጎግል የምስል ፍለጋ (google reverse image search) ውጤት እንደሚያሳየው በልጥፉ ላይ የተጠቀመው ምስል ከዋልታ ቲቪ ድህረ ገጽ የተወሰደ መሆኑን የሚያሳይ ሲሆን ትክክለኛው ምስል ርዕሰ መስተዳድሩ ግንቦት 04/2013 ዓ.ም የኢድ አል ፈጥር በዓልን በማስመልከት ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ሲያስተላልፉ የሚያሳይ ነው።

የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ርዕስቱ ይርዳው በወላይታ ጥያቄ ላይ በቅርብ ጊዜያት ውስጥ አስተያየት ስለመስጠታቸውም ሆነ አንዳች ውሳኔ እንዳንሰጥ ፌዴራል መንግሥት ጫና ያደርግብናል ስለማለታቸው የሚያስረዳ ምንም አይነት ማስረጃ የለም ፣ እንደነዚህ ያሉ መግለጫዎችን የሚያመለክቱ ምንም ዓይነት የዜና ዘገባዎችም የሉም፡፡

አርትስ ቲቪ አንዳች ውሳኔ እንዳንሰጥ ፌዴራል መንግሥት ጫና ያደርግብናል የሚለውን የፌስቡክ ልጥፍ ተመልክቶ ሐሰተኛ ሆኖ አግኝቶታል፡፡

አርትስ ቲቪ ጁንታው (ህወሓት) አንዋጋም ያሉትን የትግራይ ወጣቶችን እረሸናቸው በሚል የተለጠፈው የፌስቡክ ምስል ተመልክቶ ሐሰተኛ መሆኑን አረጋግጧል፡፡

.           .            .           .            .

ይህ ልጥፍ በፌስቡክ እና በተለያዩ የማህበራዊ ድረ ገጾች ላይ የፔሳቼክ የእውነታ መርማሪዎች በተከታታይ የሚያደርጉት የመረጃ ማረጋገጥ እና የተሳሳተ መረጃን የማጋለጥ ተግባር አካል ነው::

እንደ ፔሳቼክ ያሉ ገለልተኛ ሶስተኛ ወገን የእውነት መርማሪ ድርጅቶች ከፌስቡክ እና የማህበራዊ ድረ ገጾች ጋር በመጣመር የሃሰት ዜናን መለየት እንዲያስችልዎ ይሰራሉ:: ይህን የምናደርገውም በየማህበራዊ ድረ ገጾች ላይ የሚመለከቱት ልጥፍ/ መረጃ መነሻቸውን በማያያዝ እና ጠለቅ ያለ ዕይታ እንዲኖርዎ በማድረግ ነው::

በፌስ ቡክ ላይ የሐሰተኛ መረጃ ወይም የተጭበረበረ የመሰልዎ አጋጣሚ አለ?እንግድያውስ በእዚህ መንገድ ጥቆማ መስጠት ይችላሉ::እንዲሁም ይህን ተጨማሪ ኢንፎርሜሽን በመጠቀም አጠራጣሪ መልዕክቶችን ለመለየት የፔሳቼክ መንገዶችን ማየት ይችላሉ::

https://miro.medium.com/max/400/0*w5yMtCGA1dJdWsaN

ይህ የእውነታ ምርመራ በአርትስ ቲቪ የእውነት መርማሪ ረደኤት አበራ ተጽፎ በፔሳቼክ /አዘጋጅ ኤደን ብርሃኔ አርትኦት የቀረበ ነው::

አንቀጹ ለህትመት እንዲበቃ ያረጋገጠው ደግሞ የፔሳቼክ /አዘጋጅ ኤኖክ ናያርኪ ነው::

https://miro.medium.com/max/394/0*W96t_rnxwPEV6GVv

ፔሳቼክ የምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ የፋይናንስ መረጃ መርማሪ ተቋም ነው :: ካትሪን ጊቼሩ እና ጀስቲን አርንስቴን በተባሉ ሰዎች የተመሰረተ እንዲሁም በአህጉሪቱ ትልቁ የሲቪክ ቴክኖሎጂ እና የጋዜጠኝነት መረጃ ቋት አቅራቢ በኮድ አፍሪካ የተገነባ ነው:: እንደ ጤና : የገጠር ልማት እና የንጹህ ውሃ አቅርቦት በመሳሰሉ መስኮች ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ከመንግስት የሚጠበቁ አቅርቦቶች ላይ የተጨባጩን ዓለም እይታችንን ሊቀርጹ የሚችሉ በይፋ በሚሰራጩ የፋይናንንስ መረጃዎችን ዙርያ ህብረተሰቡ እውነተኛ መረጃን ማገናዘብ እንዲችል ለማገዝ የሚያስችል ድጋፍ ይሰጣል:: ፔሳቼክ ሚድያዎች የሚያቀርቡትን ጥንቅርም ይፈትናል:: የበለጠ መረጃ ለማግኘት pesacheck.org. ይጎብኙ::

https://miro.medium.com/max/60/0*YkqT49Yqdeot06Pp?q=20
https://miro.medium.com/max/70/0*YkqT49Yqdeot06Pp

Follow Us

https://miro.medium.com/max/54/0*mDTpdvUOWw1Vdz82?q=20
https://miro.medium.com/max/61/0*mDTpdvUOWw1Vdz82

Like Us

https://miro.medium.com/max/60/0*3pOdHCEnn3ovvbS_?q=20
https://miro.medium.com/max/72/0*3pOdHCEnn3ovvbS_

Email Us

ፔሳቼክ ኮድ ፎር አፍሪካ ከዶቼቬለ አካዳሚያ ባገኘው ድጋፍ እና ከሌሎች የአፍሪካ ሚድያዎች እንዲሁም የሲቪክ ተቋማት ጋር በመተባበር ኢኖቬት አፍሪካ ፈንድ በሚለው መስመሩ የሚያቀርበው እንቅስቃሴ ነው::

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button