FACT CHECK

ሐሰት: ይህ ምስል የተከዜ ኃይል ማመንጫ ግድብ በድሮን መመታቱን አያሳይም።

የተከዜ ኃይል ማመንጫ ግድብ ላይ ምንም አይነት በከባድ የጦር መሳርያ የደረሰ ጉዳት የለም።

በአማርኛ የተጻፈው ልጥፍ “#ሰበር #ዜና

የተከዜ ኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድብ በድሮን ተመታ

በዶክተር አብይ አህመድ የሚመራው ቡድን የተከዜ የኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድብ በሰዉ አልባ አዉሮፕላን (ድሮን) እንደመታ ተገለፀ።

የህውሓት ስራ አስፈፃሚ አባል አቶ ጌታቸዉ ረዳ በቲዊተር ገፃቸዉ እንደገለፁት ከሆነ ዛሬ ጣዋት አከባቢ ጥቃቱ በግድቡ ላይ ተፍፈጽምዋል።

የትግራይ ህዝብ የሚገለገልባቸዉን መሰረተ ልማቶችን የማጥፋት እና ህዝቡን የማንበርከክ አለማ ያነገበዉ የፋሽስቱ ቡድን በተደጋጋሚ በትግራይ ከተሞች በነዋሪዎች እና መሰረተ ልማት ያነጣጥረ ጥቃት እየፈጸመ ይገኛል።

ይህ ተስፋ ከቆረጠ ሥርዓት የተሰነዘረ የተስፋ መቁረጥ ርምጃ መሆኑን የገለፁት አቶ ጌታቸዉ ፋሽስቱ ቡድን በቀቢፀ ተስፋ የትግራይ፣የአፋር ፥የአማራ እና የኦሮሚያ ክልሎችን ንፁሓን እየደበደበ ይገኛል።” ይላል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በፈስቡክ ግፁ ህዳር 21 ቀን 2014 ዓ.ም እንደገለፀው የተከዜ የውሃ ኃይል ማመንጫ ግድብ በመንግስት ተመቷል በሚል በድጋሚ የተናፈሰው ወሬ ሀሰት ነው ብሏል። 

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ግፁ እንደገለፀው: ከዚህ ቀደምም ግድቡ ተመቷል በሚል በጥፋት ቡድኑ ተመሳሳይ የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ተሰራጭቶ እንደነበር ይታወሳል።

በመንግስት የተመታው የተከዜ ግድብ ሳይሆን ተከዜን ተሻግሮ ወረራ የፈፀመው የሽብር ቡድኑ ነው።

ይሁንና የተከዜ ግድብ ባለፈው ክረምት ሙሉ በመሆኑ ውሃውን እንዲፈስ በማድረግ የሀሰት ፕሮፓጋንዳውን እውነት ለማስመሰል ጥረት ሊያደርግ እንደሚጥር ይገመታል።

የኃይል ማመንጫ ጣቢያው ሙያተኛ ባልሆኑ ሰዎች፣  ከታለመለት ዓላማ ውጪ እንዲሰራ ከተደረገ ከፍተኛ መጠን ያለው ጉዳት ሊደርስበት እንደሚችል ይታመናል።

በመሆኑም  የሽብር ቡድኑ ህዝብን ለማሸበርና ዓለም አቀፍ ትኩረት ለመሳብ ውሃውን ሊለቅ ስለሚችል በግድቡ የታችኛው ተፋሰስ አካባቢ በተለይም በጣንቋ አበርገሌ፣ በጠለምት፣ በቃፍታ ሁመራ፣ በጠገዴ፣ በአበርገሌና በወልቃይት አካባቢዎች   የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ይህ መረጃ የደረሳችሁ የህብረተሰብ ክፍሎች መልዕክቱን በማስተላለፍ ትብብር እንድታደርጉ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

የተከዜ የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ  ሙሉ በሙሉ በሽብርተኛ ቡድኑ ቁጥጥር ስር ከመዋሉ በፊት በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ መለዋወጫ ተሟልቶለትና ከሁለት መቶ በርሜል በላይ የተርባይን ዘይት አቅርቦት ቀርቦለት በጥሩ ሁኔታ አገልግሎት በመስጠት ላይ ነበር።

ልጥፉ የተከዜ ኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድብ በድሮን ተመታ በሚል የተከዜ ኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድብ በግንባታ ላይ እያለ የነበረበትን ሁኔታ ከሚያሳይ ምስል ጋር አቅርቧል።

የያንዴክስ የምስል ፍለጋ (Yandex image search) ውጤት እንደሚያሳየው ይህ ምስል እ.ኤ.አ ሐምሌ 15 ቀን 2007 ዓ.ም ፍሊከር ከተሰኘ ድህረ ገፅ የተወሰደ ሲሆን፣ ምስሉ አሁን ግድቡ ያለበትን ትክክለኛ ሁኔታ አስያሳይም።

ይህ አይነት የሐሰት መረጃ ከዚህ በፊት በማህበራዊ ድህረገትስኦች ላይ ሲዘዋወር የነበረ ሲሆን እ.ኤ.አ በህዳር 13- 2020 ይህን የሐሰት መረጃ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን እንዲሁም እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ ዘገባን ጠቅሰው መረጃው ሐሰት መሆኑን ገልፀው ነበር።

አርትስ ቲቪ የተከዜ ኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድብ በድሮን ተመታ በሚል የተለጠፈው የፌስቡክ ልጥፍ ተመልክቶ ሐሰተኛ መሆኑን አረጋግጧል፡፡

.           .            .           .            .

ይህ ልጥፍ በፌስቡክ እና በተለያዩ የማህበራዊ ድረ ገጾች ላይ የፔሳቼክ የእውነታ መርማሪዎች በተከታታይ የሚያደርጉት የመረጃ ማረጋገጥ እና የተሳሳተ መረጃን የማጋለጥ ተግባር አካል ነው::

እንደ ፔሳቼክ ያሉ ገለልተኛ ሶስተኛ ወገን የእውነት መርማሪ ድርጅቶች ከፌስቡክ እና የማህበራዊ ድረ ገጾች ጋር በመጣመር የሃሰት ዜናን መለየት እንዲያስችልዎ ይሰራሉ:: ይህን የምናደርገውም በየማህበራዊ ድረ ገጾች ላይ የሚመለከቱት ልጥፍ/ መረጃ መነሻቸውን በማያያዝ እና ጠለቅ ያለ ዕይታ እንዲኖርዎ በማድረግ ነው::

በፌስ ቡክ ላይ የሐሰተኛ መረጃ ወይም የተጭበረበረ የመሰልዎ አጋጣሚ አለ?እንግድያውስ በእዚህ መንገድ ጥቆማ መስጠት ይችላሉ::እንዲሁም ይህን ተጨማሪ ኢንፎርሜሽን በመጠቀም አጠራጣሪ መልዕክቶችን ለመለየት የፔሳቼክ መንገዶችን ማየት ይችላሉ::

https://miro.medium.com/max/400/0*w5yMtCGA1dJdWsaN

ይህ የእውነታ ምርመራ በአርትስ ቲቪ የእውነት መርማሪ ረደኤት አበራ ተጽፎ በፔሳቼክ /አዘጋጅ ኤደን ብርሃኔ አርትኦት የቀረበ ነው::

አንቀጹ ለህትመት እንዲበቃ ያረጋገጠው ደግሞ የፔሳቼክ /አዘጋጅ ኤኖክ ናያርኪ ነው::

https://miro.medium.com/max/394/0*W96t_rnxwPEV6GVv

ፔሳቼክ የምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ የፋይናንስ መረጃ መርማሪ ተቋም ነው :: ካትሪን ጊቼሩ እና ጀስቲን አርንስቴን በተባሉ ሰዎች የተመሰረተ እንዲሁም በአህጉሪቱ ትልቁ የሲቪክ ቴክኖሎጂ እና የጋዜጠኝነት መረጃ ቋት አቅራቢ በኮድ አፍሪካ የተገነባ ነው:: እንደ ጤና : የገጠር ልማት እና የንጹህ ውሃ አቅርቦት በመሳሰሉ መስኮች ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ከመንግስት የሚጠበቁ አቅርቦቶች ላይ የተጨባጩን ዓለም እይታችንን ሊቀርጹ የሚችሉ በይፋ በሚሰራጩ የፋይናንንስ መረጃዎችን ዙርያ ህብረተሰቡ እውነተኛ መረጃን ማገናዘብ እንዲችል ለማገዝ የሚያስችል ድጋፍ ይሰጣል:: ፔሳቼክ ሚድያዎች የሚያቀርቡትን ጥንቅርም ይፈትናል:: የበለጠ መረጃ ለማግኘት pesacheck.org. ይጎብኙ::

https://miro.medium.com/max/60/0*YkqT49Yqdeot06Pp?q=20
https://miro.medium.com/max/70/0*YkqT49Yqdeot06Pp

Follow Us

https://miro.medium.com/max/54/0*mDTpdvUOWw1Vdz82?q=20
https://miro.medium.com/max/61/0*mDTpdvUOWw1Vdz82

Like Us

https://miro.medium.com/max/60/0*3pOdHCEnn3ovvbS_?q=20
https://miro.medium.com/max/72/0*3pOdHCEnn3ovvbS_

Email Us

ፔሳቼክ ኮድ ፎር አፍሪካ ከዶቼቬለ አካዳሚያ ባገኘው ድጋፍ እና ከሌሎች የአፍሪካ ሚድያዎች እንዲሁም የሲቪክ ተቋማት ጋር በመተባበር ኢኖቬት አፍሪካ ፈንድ በሚለው መስመሩ የሚያቀርበው እንቅስቃሴ ነው::

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button