Uncategorized

የታሪፍ ማሻሻያው ይፋ እስኪሆን በነበረው የታሪፍ ዋጋ አገልግሎቱ ይቀጥላል::

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2014 የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ላይ የታሪፍ መጠን እንደሚሻሻል የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ ። የዓለም ዐቀፍ ነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋ እየጨመረ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ በታኅሣሥ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ አዲስ የዋጋ ማስተካከያ መደረጉን ቢሮው አስታውሷል፡፡ ይህንን ተከትሎ በከተማዋ የትራንስፖርት አገልግሎት የታሪፍ ማሻሻያ ለማድረግ ጥናቱ እየተጠናቀቀ ነው ያለው ቢሮው፤ በቀጣይ ቀናት ይፋ ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ ነው ብሏል፡፡


ሆኖም የታሪፍ ማሻሻያው ይፋ እስኪሆን ፤ቀደም ሲል በነበረው የታሪፍ ዋጋ አገልግሎቱ እንዲቀጥል አሳስቧል፡፡ ቢሮው በከተማዋ በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ አሽከርካሪዎች የታሪፍ መጠኑ ይፋ ሳይሆን ምንም አይነት የዋጋ ጭማሪ ባለማድረግ አገልግሎት በመስጠት ሃላፊነታቸው እንዲወጡ አሳስቧል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button