loading
አዲሱ የትራንስፖርት አገልግሎት የታሪፍ ማሻሻያ ይፋ መሆን…

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2014 በቅርቡ የተደረገውን የነዳጅ ዋጋ ማስተካከያን ተከትሎ የትራንስፖርት አገልግሎት የታሪፍ ማሻሻያ መደረጉን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ገለጸ፡፡ በዚህም መሰረት በሚኒ ባስ እና በሚዲ ባስ ተሸከርካሪዎች ከ50 ሳንቲም እስከ 3 ብር ከ50 ሳንቲም ጭማሪ ስለመደረጉ ተነግሯል፡፡ ጭማሪው ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን ከታሪፍ በላይ ክፍያ የሚጠይቁ አገልገሎት ሰጭዎች ካጋጠሙ ማህበረሰቡ ለሚመለከተው አካል […]

የመመስረቻ መስፈርት አሟልተው የተገኙ ስምንት አዳዲስ ባንኮች ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፈቃድ ተሰጣቸው፡፡

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2014 የመመስረቻ መስፈርት አሟልተው የተገኙ ስምንት አዳዲስ ባንኮች ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፈቃድ ተሰጣቸው፡፡በፋይናንስ ዘርፉ ተግባራዊ እየተደረጉ ያሉ ለውጦችን ተከትሎ በርካታ ባንኮች የመመስረቻ ፈቃድ ለማግኘት ጥያቄ እያቀረቡ መሆኑ ተገልጿል፡፡ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የባንክ ቁጥጥር ዳይሬክተር ፍሬዘር አያሌው ባንክ ለመመስረት የሚያስፈልገው ዝቅተኛ የካፒል መጠን ከ500 ሚሊዮን ወደ 5 ቢሊዮን ብር ከፍ መደረጉን አስታውሰው […]

ሞሳድ የኢራኑን ፕሬዚዳንት ለመግደል አሲሯል-የኢራን የስለላ ምንጮች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2014 እስራኤል የኢራኑን ፕሬዚዳንት ለመግደል ማቀዷን ደርሸበታለሁ ሲል የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ አስታወቀ፡፡ ቴልአቪቭ ይህን የምታርገው በኢራን መረጋጋት እንዳይፈጠር ለማድረግ መሆኑንም አብዮታዊ ዘቡ አብራርቷል፡፡ ተቋሙ በይፋዊ የቴሌግራም ቻናሉ ባሰፈረው ጽሁፍ የእስራኤሉ የስለላ ድርጅት ሞሳድ የኢራኑ ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራይሲ ከቴህራን ውጭ በሚገኙበት ወቅት ግድያው እንዲፈጸምባቸው እቅድ መንደፉን የደህንነት መረጃ ያላቸው ምንጮች ነግረውኛል […]

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከጣሊያኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሉዊጂ ዲ ማዮ ጋር በሀገራዊና ቀጠናዊ ዳዮች ዙሪያ ተወያዩ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 6 ፣ 2014 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከጣሊያኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሉዊጂ ዲ ማዮ ጋር በሀገራዊና ቀጠናዊ ዳዮች ዙሪያ ተወያዩ፡፡ ሁለቱ መሪዎች ባደረጉት ውይይት የኢትዮጵያና ጣሊያን ታሪካዊ የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡ የጣሊያኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሉዊጂ ዲ ማዮ በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ምሽት አዲስ አበባ […]

ከ6 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ካፒታል ስራውን የሚጀምረው አማራ ባንክ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 6 ፣ 2014 አማራ ባንክ አክሲዮን ማህበር በሳምንቱ መጨረሻ ሥራውን በይፋ እንደሚጀምር ይፋ አደረገ፡፡ ባንኩ በ6 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር መነሻ ካፒታል ሰኔ 11 ቀን 2014 ዓ.ም ስራውን በይፋ እንደሚጀምር ነው ያስታወቀው፡፡ የባንኩን ስራ የመጀመር ሂደትን አስመልክቶ የባንኩ ከፍተኛ አመራሮች መግለጫ ጋዜጣዊ ሰጥተዋል። በ6 ቢሊዮን 516 ሚሊዮን ብር በላይ በተከፈለ የመነሻ […]

ሞስኮን ያልበረገራት የምእራባዊያን የነዳጅ ማእቀብ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 6 ፣ 2014 በሩሲያ ላይ የተጣለው የነዳጅ ግብይት ማእቀብ ግቡን እዳልመታ የሚገልጽ አዲስ ሪፖርት ይፋ ሆነ፡፡ ሪፖርቱ ፕሬዚዳንት ቭላደሚር ፑቲን ጦራቸውን ወደ ዩክሬን ባዘመቱ በ100 ቀናት ውስጥ ሞስኮ ከነዳጅ ሽያጭ 98 ቢሊዮን ዶላር ማግኘቷን ይገልጻል፡፡ ይህን ሪፖርት ይፋ ያደረገው ተቀማጭነቱ ፊንላንድ የሆነ በኢነርጂና ንጹህ አየር ላይ ምርምር የሚያደርግ ገለልተኛ ተቋም ነው […]

የትምህርትን የጥራት ችግር ለመፍታት በልዩ ትኩረት ይሰራል-ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2014 በትምህርት ስርአቱ ላይ የሚስተዋለውን የጥራት ችግር ለመፍታት የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ። ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች አዲስ ከተመደቡት የከፍተኛ ትምህርት የቦርድ አመራሮች ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው፡፡ፕሮፌሰር ብርሃኑ በዘርፉ የአምስት አመት ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫዎች መካከል የከፍተኛ ትምህርት አግባብነት እና ጥራት ማረጋገጥ በመሆኑ […]

ትራምፕ እንዲከሰሱ ድምፅ የሰጡት ተወካይ በምርጫ መሸነፍ…

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2014 በካፒቶል ህንፃ በተነሳው ግርግር ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እንዲከሰሱ ድምፅ የሰጡት የሪፓበሊካን ተወካይ በዳግም ምርጫ ተሸነፉ፡፡ በኖርዝ ካሮላይና ለአምስት ዓመታት በህግ አውጭ ምክር ቤት ተወካይነት ያገለገሉት ቶም ራይስ የተሸነፉት በቀድሞው ፕሬዚዳንት በሚደገፉት ሩሴል ፍራይ በተባሉ እጩ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ ፍራይ ማሸነፋቸውን ካወቁ በኋላ ባደረጉት ንግግር መራጩ ህዝብ በግልፅ ቋንቋ በካርዱ ተናግሯል፤ […]

ጥቃት አድራሾችን ከእንግዲህ አንታገሳቸውም-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2014 ጥቃት በደረሰባቸው አካባቢዎች ሰላም እና ደህንነትን መመለስ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት “በንጹሃን ዜጎች ላይ በህገወጥ እና በኢ-መደበኛ ኃይሎች የሚደርስ ጥቃት እና የዜጎችን መተዳደሪያ ማውደም ተቀባይነት የለውም” ብለዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቤኒንሻንጉል እና ኦሮሚያ ክልሎች፣ ዋና ዓላማቸው ኅብረተሰቡን ማሸበር […]

በአዲስ አበባ የ3ኛ ዙር የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት ዘመቻ በዛሬው ዕለት መሰጠት ተጀመረ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2014 ለቀጣዮቹ 10 ተከታታይ ቀናት በሚሰጠው ክትባት ዕድሜያቸው12 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸው ሁሉ አገልሎቱን እንደሚያገኙ ተገልጿል፡፡ ክትባቱ በሁሉም የመንግስት ጤና ጣቢያዎችና ሌሎች የተመረጡ ጊዜያዊ የክትባት መስጫ ጣቢያዎች በዘመቻ መልክ እንደሚሰጥ ታውቋል፡፡ በዚህ የ3ኛው ዙር የክትባት ዘመቻም መጠኑ 249 ሺህ የሚሆን የክትባት ዶዝ ለመስጠት መታቀዱን ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ […]