Ethiopia

ኑ ለኢትዮጵያና ስለድኻው ወገናችን ስንል ዝቅ እንበል -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2014 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የሚቻለውን በቀለኝነት ትተን የማይቻለውን ይቅርታ እንዘምር ሲሉ መልእክት አስተላለፉ:: ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት የጥምቀትን በዓል አስመልክተው ለክርስትና እምነት ተከታዮች ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክታቸው ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በዚሁ መልእክታቸው ፍቅራችንን፣ ትህትናችንንና ክብራችንን ለሀገራችንና ለወገናችን እናሳይ፣ በተለመደው መንገድ ብቻ ሄደን ሀገራችንን እንደማናድናት እንገንዘብ ብለዋል።


ኑ ለኢትዮጵያና ስለድኻው ወገናችን ስንል ዝቅ እንበል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሥራችንን ሀገር በማዳናችን እንጂ በጠላታችን ትዕቢት አንለካው ሲሉም አክለዋል፡፡
ፍቅር የአፍቃሪውን እንጂ የተፈቃሪውን ባህሪይ አይፈልግም ኢየሱስ ክርስቶስ የወደደን ለመወደድ የሚያበቃ ነገር ስላለን ሳይሆን እንዲሁ ነው፣ ፍቅሩ በቅድመ ሁኔታ ላይ የተመሠረተ ሳይሆን ፍጹም ፍቅር ነው በማለትም አብራርተዋል።


ፈጣሪ ለሰው ልጅ ያለውን ፍቅር ካሳየባቸው ታሪኮች አንዱ በዮሐንስ እጅ በዮርዳኖስ ወንዝ በተጠመቀ ጊዜ መሆኑን በመጥቀስ ለዚህም ነው ይህ ወቅት የመገለጥ ወቅት የሚባለው ብለዋል። እናም ኢትዮጵያ ዛሬ በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተና የሚገለጥ ፍቅር ያስፈልጋታል በማለትም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button