Tech

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ባበለጸጋቸው ስርዓቶች ውስጥ የሚተገበሩ ከ200 በላይ አገልግሎቶች በኦንላይን እየተሰጡ መሆኑን ገለጸ።

አዲስ አበበ፣ የካቲት 16፣ 2014 የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ባበለጸጋቸው ስርዓቶች ውስጥ የሚተገበሩ ከ200 በላይ አገልግሎቶች በኦንላይን እየተሰጡ መሆኑን ገለጸ። ተጨማሪ 45 የመንግስት አገልግሎቶችን በኦንላይን ለመስጠት የሚያስችሉ ስርዓቶች ለምተው መመረቃቸውን ሚኒስቴሩ አስታውሷል፡፡
ሚኒስቴሩ ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ጋር አገልግሎቶቹ ቀጣይነት ባለው መልኩ እንዲተገበሩ ለማድረግ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራሟል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታዋ ሁሪያ አሊ የመንግስት አገልግሎቶችን ቀልጣፋ ለማድረግና የዜጎችን እንግልት ለመቀነስ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። አሁን ላይ 222 አገልግሎቶች በኦንላይን እየተሰጡ መሆናቸውንና ከ100 ሺህ በላይ ዜጎች ደግሞ
በስርዓቱ ውስጥ መመዝገባቸውንም አብራርተዋል። የመንግስት የኤሌክትሮኒክ አገልግሎት የሚሰጥበትን ፖርታል እስካሁን ከ1ሚሊዮን 700 ሺህ በላይ
ሰዎች ጎብኝተውታል ተብሏል። ሚኒስቴሩ በቀጣዩዮቹ 10 ዓመታት ውስጥ 2 ሺህ 500 አገልግሎቶችን በኦንላይን ለመስጠት እቅድ ይዞ እየሰራ መሆኑን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button