Ethiopia

ህንድ 50 የሚሆኑ ቴክኖሎጂዎችን ለኢትዮጵያ ልታላምድ ነዉ፡፡

ህንድ 50 የሚሆኑ ቴክኖሎጂዎችን ለኢትዮጵያ ልታላምድ ነዉ፡፡

ህንድ ለኢትዮጵያ በምታላምደዉ ቴክኖሎጂ  ዙሪያም በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር  ዶክተር ጌታሁን መኩርያ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በዉይይቱም  የኢትዮ ህንድ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ማዕከል ምስረታን በተመለከተ  መክረዋል፡፡
በማዕከሉ  ውስጥ የሚሰጡ ቴክኖሎጂዎች እና ፈጠራዎች በግብርና፣ ምግብ አሰራር፣ ኢነርጂ፣ የቆሻሻ አወጋገድ፣ ትምህርት፣ የመረጃ ቴክኖሎጂ፣ የጤና ጥበቃ ዘርፎች ላይ ያተኮሩ መሆናቸዉ ከኢኖቪሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል፡፡
ቴክኖሎጂዎችን ለማሸጋገርና ለማስገባት በሁለቱ ሀገራት አቻ የሆኑ የቢዝነስ ተቋማት የመፍጠር እና የማገናኘት ተግባራትም ይከናዎናሉ ተብሏል ፡፡
በያዝነዉ ዓመት ሰኔ መጨረሻ በሚካሄደው የአይ.ሲ.ቲ ኤክስፖ ላይ በኢትዮ- ህንድ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ማዕከል የሚከናወኑ ተግባራት በሀገር አቀፍ ደረጃ የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር በተገኙበት ይፋ ይሆናል ተብሏል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button