World News

የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አቃቤ ህግ በዳርፉር ያለውን የክስ ሁኔታ መቋጫ ማበጀት እፈልጋለሁ አሉ፡፡

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2014 የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አቃቤ ህግ በዳርፉር ያለውን የክስ ሁኔታ መቋጫ ማበጀት እፈልጋለሁ አሉ፡፡
የፍርድ ቤቱ ዋና አቃቤ ህግ ካሪም ካህን በሄግ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የቀድሞው የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽር በቅርቡ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ወይ ተብለው ሲጠየቁ በዳርፉር ያለውን ሁኔታ መዝጋት እንደሚፈልጉ ተናግረዋል ተብሏል። የቀድሞ የሱዳን ሚሊሻ ሃላፊ አሊ ሙሀመድ አሊ- አብድ አልራህማን በዳርፉር ዙሪያ ግድያ፣ አስገድዶ መድፈር እና ማሰቃየት ሲፈፀም ተባባሪ ነበር በሚል፤ የአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የጦር ወንጀሎች የመጀመሪያ ችሎትን አስጀምሯል።


የኦማር አልበሽር ዋና አጋር ናቸው የሚባሉት አብድ- አልራህማን ከ20 አመት በፊት በነበረው ግጭት ውስጥ በነበራቸው ሚና በ31 የጦር ወንጀሎች እና በሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ክስ ቀርቦባቸዋል። የቀድሞው ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽር እና ሌሎች ሶስት ሰዎች በዳርፉር ለፈጸሙት ወንጀል አሁንም በአይሲሲ እየተፈለጉ የሚገኙ ሲሆን አልበሽር እና ሌሎች ሁለት አጋሮቻቸው ለፍርድ ቤቱ ተላልፈው ለህግ እንዲቀርቡ ቢጠየቅም እስካሁን በሱዳን ይገኛሉ።

በሽርን ወደ ለፍርድ ለማቅረብ ስለሚደረገው ጥረት የተጠየቁት ዋና አቃቤ ህግ ካሪም ካህን፤ ከካርቱም ወታደራዊ መንግስት ጋር የሚደረገው ድርድር እንደቀጠለ ቢሆንም ትብብሩ ግን ፈታኝ ሆኖብናል ብለዋል። ዋና አቃቤ ህጉ ያለው ሁኔታ ተሻሽሏል ቢሉም ከሱዳን መንግስት ጋር ጥልቅ ትብብር ካልተደረገ የክስ መዝገቡን የመዝጋት አዝማሚያ አሳይተዋል ተብሏል ሲል ኤ.ኤፍ.ፒ ዘግቧል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button