World News

ሰሜን ኮሪያ በአንድ ዓመት ውስጥ 14ኛውን የባለስቲክ ሚሳኤል ሙከራ አደረገች፡፡

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26፣ 2014 ሰሜን ኮሪያ በአንድ ዓመት ውስጥ 14ኛውን የባለስቲክ ሚሳኤል ሙከራ አደረገች፡፡ ፒዮንግያንግ የአሁኑን የባለስቲክ ሚሳኤል ሙከራውን ያደረገችው የኒውክሌር መርሃ ግብሯን በከፍተኛ ፍጥነት ለማሳደግ እየሰራች መሆኗን ይፋ ባደረገች በሳምንት ውስጥ ነው ተብሏል፡፡ ፕሬዚዳንት ኪም ጆንግ ኡን ሀገራቸው እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ከ2017 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ አህጉር አቋራጭ ሚሳኤል ባስወነጨፈች በአንድ ወር ጊዜ ሌላ ተመሳሳይ ሙከራ ማድረጓ ለዚህ ማሳያ ነው ተብሏል፡፡


ይህን በማድረጓም በጎረቤቷ ደቡብ ኮሪያና በአሜካ ላይ የዲፕሎማሲ ጫና እያሳደረች ነው ሲል አልጄዚራ በዘገባው አስነብቧል፡፡ የደቡብ ኮሪያ የጦር አለቆች ሁኔታውን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ የሰሜን ኮሪያን እንስቃሴ በቅርበት እየተከታተሉት እንደሆነ በማስታወስ ሊፈጠር ስለሚችለው ስጋት ሁሉ በቂ ዝግጅት እያደረግን
ነው ብለዋል፡፡


የፒዮንግያንግ ተግባር የመንግስታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ህግን የሚጥስ ነው ያለው መግለጫው በአጠቃላይ የኮሪያ ልሳነ ምድር እንዳይረጋጋ ምክንያት እንደሚሆንም አብራርቷል፡፡ ሰሜን ኮሪያ ያስወነጨፈችው ባለስቲክ ሚሳኤል በ780 ኪሎ ሜትር ከፍታ 470 ኪሎሜትሮችን የተጓዘ ሲሆን ፍጥነቱ ደግሞ ከድምፅ በ11 እጥፍ እንደሚበልጥ ነው የተገለጸው፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button