EthiopiaPoliticsRegionsSocial

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከሰሞኑ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የተፈጸመውን ድርጊት አወገዘች።

ቤተክርስትያንዋ ሰባት አብያተ ክርስትያናት ሙሉ በሙሉ ተቃጥለው የካህናት ህይዎት ማለፉንም ተናግራለች።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያሪክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ዛሬ በሰጡት መግለጫ በሶማሌ ክልል በተፈጸመው ድርጊት ሳቢያ የሰው ህይዎት በመጥፋቱ ማዘናቸዉን ተናግረዋል።
ከዚህ ባለፈም የሰላማዊ ሰዎች ህይዎት ማለፉንና በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች መፈናቀላቸውን ጠቅሰው፥ በሁኔታው የተሰማቸውን ሃዘን ገልጸዋል።
አሁን ላይ አብረው በኖሩ ወንድማማች ህዝቦች መካከል የተፈጠረው ችግር በአስቸኳይ ሊቆም እንደሚገባም አሳስበዋል ።
ቤተ ክርስቲያኒቱም የተፈጠረው ችግር እንዲቆምና ሰላም እንዲሰፍን እንደ ወትሮው ሁሉ ድጋፏን ታደርጋለች ብለዋል። ህይዎታቸውን ላጡ ወገኖችም በሁሉም አድባራትና ገዳማት ፍትሃት ይደረጋልም ብለዋል።
ከዚህም በተጨማሪም ነገ የሚጀምረው የፍልሰታ ጾም በሁሉም አድባራት እና ገዳማት በምህላ እና በጸሎት እንደሚታሰብ ገልጸዋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button