Ethiopia

በባንኮች ላይ እተፈጸመ ያለው የማጭበርበር ወንጀል አሳሳቢ ሆኗል-ፍትህ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2014 ፍትህ ሚኒስቴር በጥናት ደረስኩበት ያለውን በባንኮች ላይ የተፈጸመ የማጭበርበር ወንጀል ይፋ አደረገ፡፡ ሚኒስቴሩ በጉዳዩ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ባደረገው ውይይት ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ በተደረገ የዳሰሳ ጥናት በባንኮች ላይ ከ370 ቢሊዮን ብር በላይ የማጭበርበር ወንጀል ሙከራ ተደርጓል ብሏል። በዚህም በተለያዩ ባንኮች ከ1 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር በላይ ምዝበራ እንደተፈጸመባቸው ነው የተነገረው፡፡


ጥናቱ እንደሚያሳየው ከሆነ 50 በመቶ ማጭበርበር የተከናወነው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲሆን አቢሲኒያ፣ ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል እና ወጋገን ባንኮች እስከ 4ኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ የማጭበርበር ወንጀል ተፈፅሞባቸዋል፡፡ የፍትህ ሚኒስትር ዴኤታ ፈቃዱ ጸጋ በባንኮች ላይ የሚፈጸሙ የማጭበርበር ወንጀሎች ከጊዜ ወደ ጊዜ
እየጨመረ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡


በባንኮች ላይ የማጭበርበር ወንጀሎች መፈጸማቸው የተረጋገጠ ቢሆንም የህዝብን ገንዘብ በሚፈለገው ልክ ማስመለስ እንዳልተቻለም ገልጸዋል። ፍትህ ሚኒስቴር የማጭበርበር ወንጀል ሙከራዎቹ እየጨመሩ መምጣታቸውን በመገንዘብ መፍትሄ ለማምጣት ጥናት ማካሄዱን በውይይቱ ወቅት ተገልጿል። የጥናት ግኝቶቹን መሰረት በማድረግ ወንጀሉን ለመከላከል አሰራርን ማዘመንና የጥንቃቄ እርምጃዎችን መውሰድ ያስችላል ተብሏል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button