Ethiopia

የተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪው የሸኔ ቡድን በምዕራብ ወለጋ በንጹሀን ዜጎች ላይ ያደረሰውን አደጋ በፅኑ አወገዘ፡

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2014 የተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪው የሸኔ ቡድን በምዕራብ ወለጋ በንጹሀን ዜጎች ላይ ያደረሰውን አደጋ በፅኑ አወገዘ፡፡ ምክር ቤቱ የሽብር ቡድኑ በጸጥታ ሀይሎች ጥቃት እየደረሰበት በመሆኑ ከጥቃቱ በመሸሽ በምዕራብ ወለጋ ንጹሀን ዜጎች ላይ አደጋ አድርሷል ብሏል። በኦሮሚያ ክልል፣ ቄለም ወለጋ ዞን የሚገኙ ንጹሀን ዜጎቻችን ላይ የፈጸመው ጭፍጨፋ በእጅጉ የሚወገዝ መሆኑን አስታውቋል፡፡


በዜጎቻችን ላይ በደረሰው ስቃይ እና መከራ እያዘንን ይሄንን አሸባሪ ቡድን መላው ህዝባችን በተለይም የአካባቢው ማህበረሰብ ከጸጥታ ሀይላችን ጋር በመተባበር እስከመጨረሻው እናስወግደው በማለትም ምክር ቤቱ ጥሪውን አቅርቧል፡፡ በተያያዘም የኦሮሚያ ክልል መንግስት አሸባሪው የሸኔን ቡድን ለመደምሰስ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቋል፡፡ የክልሉ መንግስት አሸባሪው ሸኔ በቄለም ወለጋ ሐዋ ገላን ወረዳ በንፁኃን ላይ ባደረሰው አሰቃቂ ጭፍጨፋ
ከፍተኛ ኀዘን የተሰማው መሆኑን ጨፌው ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። በመሆኑም ኅብረተሰቡ ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት የአካባቢውን ሰላም መጠበቅ እንደሚጠበቅበት እንዲሁም የአሸባሪው ሸኔ አባላት ላይ የማያዳግም እርምጃ ሊወስድባቸው እንደሚገባም ነው ጨፌው ጥሪ ያቀረበው።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button