Ethiopia

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት 11 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወታቸው አለፈ፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 11፣2013 በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት 11 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወታቸው አለፈ፡፡ የጤና ሚኒስቴር በ24 ሰዓቱ የኮቪድ-19 ሪፖርት መረጃው ላይ እንዳስታወቀው ፤ በቫይረሱ ምክንያት 11 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፡፡ እስካሁንም በሀገሪቱ በኮሮና ምክንያት ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥርም 4 ሺህ 4 መቶ 89 ደርሷል፡፡

በ24 ሰዓታት ዉስጥ 5ሺህ 1 መቶ 73 ሰዎች ላብራቶሪ ምርመራ አድርገዉ 6 መቶ 88 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃለይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2 መቶ 89 ሺህ 9 መቶ 62 ደርሷል፡፡ በጽኑ የታመሙ ሰዎች 434 ሲሆኑ ፤ በ24 ሰዓታት ውስጥ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ደግሞ 218
ናቸዉ፡፡

አጠቃላይ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 2 መቶ 65 ሺህ 5 መቶ 89 መሆኑን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ የኮቪድ-19 ክትባት የተከተቡ ሰዎች ደግሞ 2 ሚሊዮን 3መቶ 14 ሺህ 394 ደርሷል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button