Africa

በቻድ ምርጫው እንዲደናቀፍ ቢደረግም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ እንደተሳተፈ ገዥው ፓርቲ ተናገረ ፡፡

አዲስ አበባ፣  ሚያዚያ ፡ 04፣ 2013 በቻድ ምርጫው እንዲደናቀፍ ቢደረግም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ እንደተሳተፈ ገዥው ፓርቲ ተናገረ ፡፡ በቻድ በተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ መራጮች እንዳይሳተፉ በተቃዋሚዎች ጥሪ የቀረበላቸው ቢሆንም የድምፅ አሰጣጡ በሰላማዊ መንገድ የተካሄደ መሆኑን የአፍሪካ ህብረት አስታውቋል ፡፡ እሁድ እለት የተካሄደውን የምርጫ ውጤትም ቻዳውያን እየተጠባበቁ ሲሆን የወቅቱ ፕሬዚዳንት ኢድሪስ ዴቢ ሁነኛ ተቀናቃኞች ሳይገጥሟቸው ከሰባቱ እጩ ተወዳዳሪዎች ተሽለው የ30 ዓመት ስልጣነ መንበራቸውን ያፀናሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የአፍሪካ ኒውስ ዘጋቢ በመዲናዋ ንጃሜና የምርጫ ጣቢያዎች ጸጥ ያሉ ነበሩ በማለት ቢናገርም ገዥው ፓርቲ የመራጮቹ ቁጥር ከፍተኛ እንደነበር ገልጧል፡፡ እስካሁን ግን የተሳታፉ የመራጮች ብዛት ገና በምርጫ ቦርድ ይፋ አልተደረገም ተብሏል፡፡ ቻዳውያን በምርጫ ሂደቱ እንዳይካፈሉ በተፎካካሪ ፓርቲዎች በኩል ጥሪ የቀረበ ቢሆንም የገዥው ፓርቲ አማራሮች ግን ምርጫው ያለምንም ግርግር እና እንከን እንደተጠናቀቀ አስታውቀዋል፡፡

የምርጫ ከሚሽን የድምፅ አሰጣጡ ከተጠናቀቀ በኋላ በመዲናዋ ንጃሜና የምርጫ ጣቢያ ማዕከል ቆጠራውን የጀመረ ሲሆን ጊዜያዊ ውጤቶችን ለማሳወቅ እስከ ሚያዚያ 25 ድረስ ጊዜ ያስፈልገኛል ብሏል፡፡ ፕሬዚዳንት ዴቢ በ1990 በመፈንቅለ መንግስት ስልጣንን የተቆጣጠሩ ሲሆን በ2018 ባሻሻሉት ህገ-መንግስት እስከ 2033 ድረስ በስልጣን እንዲቆይ ያስችለዋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button