Politics

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በዳቮስ ኢኮኖሚክ ጉባኤ ላይ ንግግር አደረጉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በዳቮስ ኢኮኖሚክ ጉባኤ ላይ ንግግር አደረጉ

በንግግራቸው በኢትዮጵያ ስለተጀመሩት ለውጦች ዳሰሳ አድርገዋል

በአለም ኢኮኖሚ ጉባኤ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ጠቅለዓይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መደመር ያለፈ ፀጋችንን እንደገና የመፈተሸና ወደ ብልጽግና የመመለስ መርኅ ነው ብለዋል።

ዴሞክራሲ፣ ምጣኔ ሀብታዊ ማሻሻያና ቀጠናዊ ውሕደት የለውጥ ምሕዋራችን የቆመባቸው ዓምዶች ሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡

ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሕገ-መንግሥታዊ ቃል-ኪዳንን ለማክበር እየሠሩ መሆናቸውን ያስታወቁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ‹‹ባለፉት ዘጠኝ ወራት በሺዎች የሚቆጠሩ የፖለቲካ እስረኞችን ፈትተናል፤ በግዞት የነበሩ ፖለቲከኞችንና መገናኛ ብዙኃንን ወደ ሀገራቸው እንዲገቡ አድርገናል፡፡ በዚህም ለውጥ እያዬን ነው›› ብለዋል፡፡

በምጣኔ ሀብት ዘርፉ ኢትዮጵያን የዓለም ምጣኔ ሀብት ማዕከል እንድትሆን እየሠሩ መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡ ሴቶችና ወጣቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የምጣኔ ሀብት ሥርዓት እየዘረጋን ነው ብለዋል፡፡

ሴቶች በሀገራችን ዋና ዋና የሚኒስትር ቦታዎች ተሰይመዋል፤ የፆታ ስብጥርንም አመጣጥነናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በዘመናዊት ኢትዮጵያ የመጀመሪያዋን ሴት ርዕሰ ብሔር ብንመርጥም ይህ ብቻ ግን በቂ አይደለም ነው ያሉት።

የ100 ሚሊዮኖች ሀገር ኢትዮጵያ አሁንም ወጣትና አምራች ዜጎቿን ያላረካች በመሆኑ በትምህርትና መሠል የሰብዓዊ ልማቶች ላይ በትኩረት ልንሠራ እየተዘጋጀን ነው ሲሉም ለፎረሙ ተሳፊዎች ገልጸዋል፡፡

ለውጥ መጥቷል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሁን ሀገራችን ላይ ትልቅ ተስፋ አለ፡፡ በሁሉም መስክም እያንሰራራን ነው በማለት ለታዳሚው ኢትዮጵያ ያለችበትን ሁኔታ አስታውቀዋል።

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button