Africa

ዲሞክራቲክ ኮንጎ በሀገሯ የሚገኙ ዲፕሎማቶች ከመንግስ እውቅና ውጭ ከዋና ከተማዋ እንዳይወጡ ከለከለች፡፡

አዲስ አበባ፣የካቲት 18፣ 2013 ዲሞክራቲክ ኮንጎ በሀገሯ የሚገኙ ዲፕሎማቶች ከመንግስ እውቅና ውጭ ከዋና ከተማዋ እንዳይወጡ ከለከለች፡፡ ሀገሪቱ በዲፕሎማቶች ላይ ይህን እገዳ የጣለችው ሰሞኑን ለጉብኝት ከከተማ ውጭ ሲጓዙ የነበሩት የጣሊያኑ አምባሳደር መገደላቸውን ተከትሎ ነው፡፡ በዚህም መሰረት ማንኛውም የዲፕሎማቲክ ሚሽን አባላት ከዋና ከተማዋ ኪንሻሳ ለመውጣት ሲፈልጉ ቀድመው ለመንግስት ማሳወቅ ይኖርባቸዋል፡፡

አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው ፕሬዚዳንት ፊሊክስ ሺኬሴዲ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሱት ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸው፣ ከምክትል መከላከያ ሚኒስትሩና ከደህንነት ሰዎቻቸው ጋር ልዩ ስብሰባ ካደረጉ በኋላ ነው፡፡ ከስብሰባው በኋላ የፕሬዚዳንት ልዩ አማካሪ አምበሳደሩን ሲያጓጓዝ አብሮ የተገደለውን አሽከርካሪ ቤተሰቦችን ጎብኝተዋል፡፡ የፀጥታ ችግር የሚበዛባት የሰሜናዊ ኪቩ ግዛት አስተዳዳሪ የድርጊቱን ፈፃሚዎች በምርመራ ለይተን ለፍርድ የማቅረብ ሀላፊነት አለብን ይህንንም ለወዳጃችን ጣሊያን ማረጋጥ እንፈልጋለን ብለዋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button